ዘፀአት 29:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አውራውንም በግ ታርደዋለህ፤ ደሙንም ወስደህ በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ትረጨዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አውራውንም በግ ዕረደው፤ ደሙንም ወስደህ በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ርጨው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አውራውን በግ ታርደዋለህ፥ ደሙንም ወስደህ በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ትረጨዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱንም ዐርደህ ደሙን በመሠዊያው ጐን በአራቱም ማእዘን እርጨው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አውራውንም በግ ታርደዋለህ፥ ደሙንም ወስደህ በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ትረጨዋለህ። |
አውራውንም በግ በየብልቱ ትቈርጠዋለህ፤ የሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ ታጥባለህ፤ ከብልቱና ከራሱም ጋር ታኖረዋለህ።
በሬውንም በእግዚአብሔር ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን ያቀርባሉ፤ ደሙንም በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።
እጁንም ለቍርባን በቀረበው ራስ ላይ ይጭናል፤ በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ አጠገብ ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በሚቃጠለው መሥዋዕት፥ በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።