La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 28:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከላ​ይም በመ​ካ​ከል አን​ገ​ትጌ ይሁ​ን​በት፤ እን​ዳ​ይ​ቀ​ደ​ድም በግ​ብረ መርፌ የተ​ሠራ ጥልፍ በአ​ን​ገ​ት​ጌው ዙሪያ ይሁ​ን​በት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከላይ በኩል በመካከሉ ዐንገትጌ አድርገህ አብጀው፤ እንዳይቀደድም በማስገቢያው ዙሪያ እንደ ክሳድ ያለ ዝምዝም ጠርዝ ሥራለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

መሃሉ ላይ ራስ ማስገቢያ አንገትጌ ይኑረው፤ እንዳይቀደድም የአንገትጌው ዙሪያ የተጠለፈ ይሁን።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የራስ ማጥለቂያ አንገትጌም ይኑረው፤ ይህም አንገትጌ እንዳይተረተር ወደ ውስጥ ታጥፎ በእጅ ሥራ የተቀመቀመ ይሁን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከላይም በመካከል አንገትጌ ይሁንበት፤ እንዳይቀደድም እንደ ጥሩር የተሠራ ጥልፍ በአንገትጌው ዙሪያ ይሁንበት።

Ver Capítulo



ዘፀአት 28:32
9 Referencias Cruzadas  

ዖዝ​ያ​ንም ለጭ​ፍ​ራው ሁሉ ጋሻና ጦር፥ ራስ ቍርና ጥሩር፥ ቀስ​ትና የሚ​ወ​ነ​ጭ​ፉ​ትን ድን​ጋይ አዘ​ጋ​ጀ​ላ​ቸው።


ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ እኩ​ሌ​ቶቹ ብላ​ቴ​ኖች ሥራ ይሠሩ ነበር፤ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም ጋሻና ጦር፥ ቀስ​ትና ጥሩ​ርም ይዘው በፊ​ትና በኋላ ይጠ​ብቁ ነበር፤ አለ​ቆ​ቹም ከይ​ሁዳ ቤት ሁሉ በኋላ ይቆሙ ነበር።


“ቀሚ​ሱ​ንም ሁሉ ሰማ​ያዊ አድ​ር​ገው።


በታ​ች​ኛ​ውም ዘርፍ ዙሪያ ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራዊ፥ ከቀ​ይም ግምጃ ሮማ​ኖ​ችን አድ​ርግ፤ በእ​ነ​ዚ​ያም መካ​ከል በዙ​ሪ​ያው በተ​መ​ሳ​ሳይ ቅርጽ የወ​ርቅ ሮማ​ኖች ሻኵ​ራ​ዎ​ችን አድ​ርግ፤


በቀ​ሚ​ሱም መካ​ከል አን​ገ​ትጌ ነበረ፤ እን​ዳ​ይ​ቀ​ደ​ድም በአ​ን​ገ​ት​ጌው ዙሪያ በአ​ን​ድ​ነት የተ​ያ​ያዘ ጥልፍ ነበረ።


ከጥሩ በፍ​ታም መል​ካ​ሞ​ቹን ቆቦች፥ ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍ​ታም የእ​ግር ሱሪ​ዎ​ችን፥