ዘፀአት 28:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለት የወርቅ ቀለበቶችንም ሥራ፤ እነርሱንም ልብሰ መትከፉ በውስጥ በሚያልፍበት በከንፈሩ በኩል በሁለቱ የልብሰ እንግድዓ ጫፎች ላይ ታኖራቸዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አበጅተህ ከኤፉዱ ቀጥሎ ባለው በውስጠኛ ጠርዝ ላይ፣ በሌላ በኩል ካሉት ሁለት የደረት ኪስ ጐኖች ጋራ አያይዛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተህ በኤፉዱ ፊት ለፊት ባለው በደረት ኪሱ በሁለቱ ጫፎች ላይ ታደርጋቸዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተህ በውስጥ በኩል ከኤፉዱ ቀጥሎ ባለው የደረት ኪስ ከታችኛዎቹ ማእዘኖች ጋር እንዲገጣጠሙ አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለት የወርቅ ቀለበቶችም ሥራ፥ እነርሱንም በኤፉዱ ፊት ለፊት ባለው በደረቱ ኪስ በሁለቱ ጫፎች ላይ ታደርጋቸዋለህ። |
የሁለቱንም ቋዶች ጫፎች በሁለቱ ፈርጦች ውስጥ አግብተህ በልብሰ መትከፉ ጫንቃዎች ላይ በስተፊት በመጋጠሚያቸው ታደርጋቸዋለህ።
ደግሞም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሥራ፤ በልብሰ መትከፉ ፊት ከጫንቃዎች በታች በብልሃት ከተጠለፈ ከልብሰ መትከፉ ቋድ በላይ በመጋጠሚያው አጠገብ ታደርጋቸዋለህ።
የዔሊ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ፥ የዮካብድ ወንድም፥ የአኪጦብ ልጅ በሴሎ ለእግዚአብሔር ካህን የሆነ፥ ኤፉድም የለበሰ አኪያ አብሮ ነበር፤ ሕዝቡም ዮናታን እንደ ሄደ አላወቁም ነበር።