በቅርጽ ሠራተኛ ሥራ እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በሁለት ድንጋዮች ቅረጽ፤ በወርቅም ፈርጥ አድርግ።
ዘፀአት 28:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርጦችንም ከጥሩ ወርቅ ሥራ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወርቅ ፈርጦችን አብጅ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርጦችን ከወርቅ ሥራ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለት የወርቅ ፈርጦች ሥራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወርቅም ፈርጦች ሁለትም ድሪዎች ከጥሩ ወርቅ ሥራ፤ እንደ ተጎነጎነም ገመድ አድርግ፤ የተጎነጎኑትንም ድሪዎች በፈርጦቹ ላይ አንጠልጥል። |
በቅርጽ ሠራተኛ ሥራ እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በሁለት ድንጋዮች ቅረጽ፤ በወርቅም ፈርጥ አድርግ።
ሁለት ቋዶችንም ከጥሩ ወርቅ እንደ ተጐነጐነ ገመድ አድርገህ ሥራ፤ የተጐነጐኑትንም ቋዶች በፈርጦቹ ላይ አንጠልጥል።
ሁለትም የወርቅ ፈርጦች፥ ሁለትም የወርቅ ቀለበቶች ሠሩ፤ ሁለቱንም የወርቅ ቀለበቶች በልብሰ እንግድዓው በሁለቱ ወገን አደረጉ።
ልብሰ እንግድዓውን ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ፥ እንደ ልብሰ መትከፉ አሠራር ከወርቅና ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ፥ ከተፈትለም ከጥሩ በፍታ አደረጉ።