ዘፀአት 28:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቅርጽ ሠራተኛ ሥራ እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በሁለት ድንጋዮች ቅረጽ፤ በወርቅም ፈርጥ አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእጅ ጥበብ ባለሙያ ማኅተም እንደሚቀርጽ የእስራኤልን ልጆች ስም በሁለቱ ድንጋዮች ላይ ቅረጽ፤ ከዚያም ድንጋዮቹን በወርቅ ፈርጥ ክፈፋቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቅርጽ ሠራተኛ ሥራ እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ የእስራኤልን ልጆች ስም በሁለት ድንጋዮች ቅረጽ በወርቅ ፈርጥ ሥራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሁለቱ ድንጋዮች ላይ የዐሥራ ሁለቱን የያዕቆብ ልጆች ስሞች ለመቅረጽም ችሎታ ያለው ብልኅ ሰው አግኝ፤ ድንጋዮቹንም ከወርቅ በተሠራ ፈርጥ ላይ አኑራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቅርጽ ሠራተኛ ሥራ እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ የእስራኤልን ልጆች ስም በሁለት ድንጋዮች ቅረጽ በወርቅም ፈርጥ አድርግ። |
ለእስራኤል ልጆችም የመታሰቢያ ድንጋዮች ይሆኑ ዘንድ ሁለቱን ዕንቍዎች በልብሰ መትከፉ ጫንቃዎች ላይ ታደርጋለህ፤ አሮንም በሁለቱ ጫንቃዎች ላይ ለመታሰቢያ ስማቸውን በእግዚአብሔር ፊት ይሸከማል።
የዕንቍም ድንጋዮች እንደ እስራኤል ልጆች ስሞች ዐሥራ ሁለት ይሆናሉ፤ በየስማቸውም ማኅተም አቀራረጽ ይቀረጹ፤ ስለ ዐሥራ ሁለቱ ነገዶችም ይሁኑ።
የሁለቱንም ቋዶች ጫፎች በሁለቱ ፈርጦች ውስጥ አግብተህ በልብሰ መትከፉ ጫንቃዎች ላይ በስተፊት በመጋጠሚያቸው ታደርጋቸዋለህ።
“ከጥሩ ወርቅም የወርቅ ቅጠል ሥራ፤ በእርሱም እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ፦ ቅድስና ለእግዚአብሔር የሚል ትቀርጽበታለህ።
“እኔ ሕያው ነኝ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን ሆይ፥ አንተን በሰወርሁበት ቀኝ እጄ እንዳለ ማሕተም ነበርህ፤ እንግዲህ ወዲህ ግን እንደማትኖር እኔ ሕያው ነኝ፤” ይላል እግዚአብሔር፤
በኢያሱ ፊት ያኖርሁት ድንጋይ እነሆ አለ፣ በአንዱ ድንጋይ ላይ ሰባት ዓይኖች አሉ፣ እነሆ፥ ቅርጹን እቀርጻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ የዚያችንም ምድር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ።
እናንተም ልትድኑበት የተማራችሁትን የእውነት ቃል ሰምታችሁና አምናችሁ፤ ተስፋ ባደረገላችሁ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ።
ሆኖም “ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፤” ደግሞም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።
የሕያው አምላክ ማኅተም ያለውም ሌላ መልአክ ከፀሐይ መውጫ ሲወጣ አየሁ፤ ምድርንና ባሕርንም ሊጐዱ ለተሰጣቸው ለአራቱ መላእክት በታላቅ ድምፅ እየጮኸ