ዘፀአት 28:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ አወላለዳቸው ስድስት ስሞችን በአንዱ ድንጋይ፥ የቀሩትንም ስድስቱን ስሞች በሌላው ድንጋይ ቅረጽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ልደታቸው ቅደም ተከተል ስድስቱን ስሞች በአንዱ ድንጋይ ላይ የቀሩትንም ስሞች በሌላው ላይ ቅረጽባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ የልደታቸው ቅደም ተከተል ስድስት ስም በአንድ ድንጋይ ላይ፥ የቀረውንም ስድስቱን ስም በሌላኛው ድንጋይ ቅረጽ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይኸውም የልደታቸውን ቅደም ተከተል ሳታፋልስ ስድስቱን በአንድ ድንጋይ ላይ፥ ስድስቱንም በሌላ ድንጋይ ላይ ጻፍ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ አወላለዳቸው ስድስት ስም በአንድ ድንጋይ፥ የቀረውንም ስድስቱን ስም በሌላው ቅረጽ። |
በቅርጽ ሠራተኛ ሥራ እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በሁለት ድንጋዮች ቅረጽ፤ በወርቅም ፈርጥ አድርግ።