ከሃያውም ሳንቆች በታች አርባ የብር እግሮችን አድርግ፤ ከእያንዳንዱ ሳንቃ በታች ለሁለት ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ይሁኑ። ከሌላውም ሳንቃ በታች ለሁለት ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ይሁኑ።
ዘፀአት 27:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምዕራብም ወገን ለአደባባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ዐሥርም ምሰሶዎች፥ ዐሥርም እግሮች ይሁኑለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የአደባባዩ ምዕራብ ጫፍ ስፋቱ ዐምሳ ክንድ ሆኖ ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር መቆሚያዎች ያሉት መጋረጃዎች ይኑሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምዕራብ በኩል ላለው ለአደባባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር እግሮች ይሁኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምዕራብ በኩል አደባባይ ዐሥር እግሮች ካሉአቸው ዐሥር ምሰሶዎች ጋር ርዝመታቸው ኻያ ሁለት ሜትር የሚሆን መጋረጃዎች ይኑሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምዕራብም ወገን ለአደባባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጆች፥ አሥርም ምሰሶች፥ አሥርም እግሮች ይሁኑለት። |
ከሃያውም ሳንቆች በታች አርባ የብር እግሮችን አድርግ፤ ከእያንዳንዱ ሳንቃ በታች ለሁለት ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ይሁኑ። ከሌላውም ሳንቃ በታች ለሁለት ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ይሁኑ።
እንዲሁም በሰሜን ወገን መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ከናስ የተሠሩ ሃያ ምሰሶዎች፥ ሃያም እግሮች ይሁኑ፤ ለምሰሶዎችም በብር የተለበጡ ኩላቦችና ዘንጎች ይሁኑ።