በውጭ ከተጋጠሙት መጋረጃዎች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ አምሳ ቀለበቶች አድርግ፤ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎቹ በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ እንዲሁ አምሳ ቀለበቶች አድርግ።
ዘፀአት 26:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምስቱ መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው አንድ ሆነው ይጋጠሙ፤ ስድስቱም መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው አንድ ሆነው ይጋጠሙ፤ ስድስተኛውም መጋረጃ በድንኳኑ ፊት ይደረብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐምስቱን መጋረጃዎች በአንድ ላይ፣ እንደዚሁም ስድስቱን መጋረጃዎች በአንድ ላይ አድርገህ ስፋቸው፤ ከማደሪያው ድንኳን ፊት ለፊት ስድስተኛውን መጋረጃ ዕጠፍና በላዩ ላይ ደርበው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምስቱን መጋረጆች ለብቻ፥ ስድስቱንም መጋረጆች ለብቻ አንድ ሆነው ይጋጠሙ፤ ስድስተኛው መጋረጃ በድንኳኑ ፊት ይደረብ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምስቱን በአንድ በኩል፥ ስድስቱን በሌላ በኩል አድርገህ በአንድነት በማጋጠም ስፋቸው፤ ስድስተኛው መጋረጃ ታጥፎ ከፊት በኩል በድንኳኑ ላይ ይደረብ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምስቱ መጋረጆች አንድ ሆነው ይጋጠሙ፥ ስድስቱም መጋረጆች እርስ በርሳቸው አንድ ሆነው ይጋጠሙ፤ ስድስተኛውም መጋረጃ በድንኳኑ ፊት ይደረብ። |
በውጭ ከተጋጠሙት መጋረጃዎች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ አምሳ ቀለበቶች አድርግ፤ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎቹ በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ እንዲሁ አምሳ ቀለበቶች አድርግ።
አምስቱ መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው የተጋጠሙ ይሁኑ፤ ሌሎችም አምስት መጋረጃዎች እንዲሁ እርስ በርሳቸው የተጋጠሙ ይሁኑ።።
እያንዳንዱም መጋረጃ ርዝመቱ ሠላሳ ክንድ፥ እያንዳንዱም መጋረጃ ወርዱ አራት ክንድ ይሁን፤ የዐሥራ አንዱም መጋረጃዎች መጠናቸው ትክክል ይሁን።