አምሳም የናስ መያዣዎችን ሥራ፤ መያዣዎችንም ወደ ቀለበቶች አግባቸው፤ መጋረጃዎችንም አጋጥማቸው፤ አንድም ይሆናሉ።
ዘፀአት 26:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምሳ የወርቅ መያዣዎች ሥራ፤ መጋረጃዎችን እርስ በርሳቸው በመያዣዎች አጋጥማቸው፤ ድንኳኑም አንድ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የመገናኛው ድንኳን አንድ ወጥ ይሆን ዘንድ መጋረጃዎቹን በአንድ ላይ ለማያያዝ ዐምሳ የወርቅ ማያያዣዎችን ሥራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምሳ የወርቅ መያዣዎችን ሥራ፤ ድንኳኑም አንድ ወጥ እንዲሆን መጋረጃዎቹን እርስ በርሳቸው በመያዣዎች አጋጥማቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተቀደሰው ድንኳን አንድ ይሆን ዘንድ ለእነዚህ ሁለት ክፍሎች ኀምሳ የወርቅ መያዣዎችን ሠርተህ በቀለበቶቹ አገጣጥማቸው።። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምሳ የወርቅ መያዣዎች ሥራ፤ ማደሪያውንም አንድ እንዲሆን መጋረጆችን እርስ በርሳቸው በመያዣዎች አጋጥማቸው። |
አምሳም የናስ መያዣዎችን ሥራ፤ መያዣዎችንም ወደ ቀለበቶች አግባቸው፤ መጋረጃዎችንም አጋጥማቸው፤ አንድም ይሆናሉ።
መጋረጃውንም በምሰሶዎች ላይ ስቀለው፤ በመጋረጃውም ውስጥ የምስክሩን ታቦት አግባው፤ መጋረጃውም በቅድስቱና በቅድስተ ቅዱሳኑ መካከል መለያ ይሁናችሁ።
አምሳ ቀለበቶችን በአንድ መጋረጃ አድርግ፤ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አድርግ፤ ቀለበቶቹ ሁሉ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት ይሆናሉ።
ድንኳኑንም፥ አደባባዩንም፥ መደረቢያውንም፥ መያዣዎቹንም፥ ሳንቆቹንም፥ መወርወሪያዎቹንም፥ ምሰሶዎችንና እግሮቻቸውን፤
አምሳም የወርቅ መያዣዎችን ሠሩ፤ መጋረጃዎችንም አንዱን ከሌላው በመያዣዎች አጋጠሙአቸው፤ አንድ ድንኳንም ሆነ።
ድንኳኑንም፥ መደረቢያውንም፥ ዕቃውንም ሁሉ ወደ ሙሴ አመጡ፤ መያዣዎቹን፥ ሳንቆቹን፥ መወርወሪያዎቹን፥ ምሰሶዎቹን፥ እግሮቹንም፤
ከእርሱ የተነሣ አካል ሁሉ እያንዳንዱ ክፍል በልክ እንደሚሠራ፥ በተሰጠው በሥር ሁሉ እየተጋጠመና እየተያያዘ፥ ራሱን በፍቅር ለማነጽ አካሉን ያሳድጋል።