አምሳም የናስ መያዣዎችን ሥራ፤ መያዣዎችንም ወደ ቀለበቶች አግባቸው፤ መጋረጃዎችንም አጋጥማቸው፤ አንድም ይሆናሉ።
ዘፀአት 26:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከድንኳኑ መጋረጃዎች የቀረ ትርፍ ግማሽ መጋረጃ በድንኳኑ ጀርባ ይጋረድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ድንኳኑ መጋረጃዎች ትርፍ ቁመትም፣ ትርፍ ግማሽ መጋረጃ ከማደሪያው ድንኳን ጀርባ ላይ እንዲንጠለጠል ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከድንኳኑ መጋረጆች የቀረ ትርፍ ግማሽ መጋረጃ በማደሪያው ጀርባ ይንጠልጠል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትርፍ የሆነውን ግማሽ መጋረጃ ወስደህ በድንኳኑ ጀርባ አንጠልጥለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከድንኳኑ መጋረጆች የቀረ ትርፍ ግማሽ መጋረጃ በማደሪያው ጀርባ ይንጠልጠል። |
አምሳም የናስ መያዣዎችን ሥራ፤ መያዣዎችንም ወደ ቀለበቶች አግባቸው፤ መጋረጃዎችንም አጋጥማቸው፤ አንድም ይሆናሉ።
ድንኳኑን እንዲሸፍን ከርዝመቱ በአንድ ወገን አንድ ክንድ፤ በአንድ ወገንም አንድ ክንድ ከድንኳኑ መጋረጆች የቀረው ትርፍ በድንኳኑ ውጭ በወዲህና በወዲያ ይጋረድ።