ከእርስዋም ሌላ ቢያገባ፥ ቀለብዋን፥ ልብስዋንም፥ ለጋብቻዋም ተገቢውን ይስጣት፤ እንዳልበደላትም ምስክር ያሰማባት።
ዘፀአት 21:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለልጁም ሊድራት ቢወድድ፥ ለሴት ልጆች የሚገባውን ያድርግላት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለወንድ ልጁ ትሆን ዘንድ መርጧት ከሆነ እንደ ራሱ ልጅ የሚገባትን መብት ይስጣት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለልጁም ሊድራት ቢፈልግ፥ ለሴት ልጆች የሚገባውን ያድርግላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚስት ትሆንለት ዘንድ ለልጁ ሊሰጣት ከፈለገ ግን እንደ ሴት ልጁ አድርጎ ይቊጠራት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለልጁም ብድራት፥ ለሴት ልጆች የሚገባውን ያድርግላት። |
ከእርስዋም ሌላ ቢያገባ፥ ቀለብዋን፥ ልብስዋንም፥ ለጋብቻዋም ተገቢውን ይስጣት፤ እንዳልበደላትም ምስክር ያሰማባት።
ለእርሱ ከታጨች በኋላ ጌታዋን ደስ ባታሰኘው በዎጆ ይስደዳት፤ ነገር ግን ለሌላ ወገን ይሸጣት ዘንድ አይገባውም። እርሱ አርክሶአታልና።