በሬው ወንድን ልጅ ቢወጋ፥ ሴትንም ልጅ ቢወጋ ይህንኑ ፍርድ ያድርጉበት።
አንድ በሬ አንድን ወንድ ወይም ሴት ልጅ ቢወጋ በዚሁ ሕግ መሠረት ይፈጸም።
ወንድን ልጅ ቢወጋ ወይም ሴትን ልጅ ቢወጋ፥ ይህንኑ ፍርድ ያድርጉበት።
በሬው ወንድ ወይም ሴት ልጅ ወግቶ ቢገድል ቅጣቱ ተመሳሳይ ይሁን።
ደግሞ ወንድን ልጅ ቢወጋ ሴትንም ልጅ ቢወጋ፥ ይህንኑ ፍርድ ያድርጉበት።
“በሬም ወንድን ወይም ሴትን ቢወጋ ቢሞቱም፥ በሬው በድንጋይ ይወገር፤ ሥጋውም አይበላ፤ የበሬው ባለቤት ግን ንጹሕ ነው።
ከእርሱ ግን ካሳ ቢፈልጉ፥ የሕይወቱን ካሳ የጫኑበትን ያህል ይስጥ።
በሬው ወንድ ባሪያ ወይም ሴት ባሪያ ቢወጋ፥ የበሬው ባለቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለጌታቸው ይስጥ፤ በሬውም ይወገር።
ቆመ፥ ምድርንም አወካት፣ ተመለከተ፥ አሕዛብንም አናወጠ፣ የዘላለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ፥ የዘላለምም ኮረብቶች ቀለጡ፣ መንገዱ ከዘላለም ነው።