La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ወጣ፤ ሁለ​ቱም የዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሰዎች ሲጣሉ አየ፤ ሙሴም በዳ​ዩን፥ “ለምን ባል​ን​ጀ​ራ​ህን ትመ​ታ​ዋ​ለህ?” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በማግስቱም በወጣ ጊዜ ሁለት ዕብራውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አየ፤ ጥፋተኛውንም፣ “የገዛ ወገንህን የምትመታው ለምንድን ነው?” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሁለተኛውም ቀን ወጣ፥ ሁለት ዕብራውያን ሰዎች ሲጣሉ አየ፥ በዳዩንም፦ “ለምን ባልንጀራህን ትመታዋለህ?” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በማግስቱም ወደዚያው ስፍራ ተመልሶ ሲሄድ ሁለት ዕብራውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አየ፤ በደል የሠራውንም ሰው ተመልክቶ “ወገንህ የሆነውን ዕብራዊ ለምን ትመታዋለህ?” ሲል ጠየቀው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሁለተኛውም ቀን ወጣ፤ ሁለቱም የዕብራውያን ሰዎች ሲጣሉ አየ፤ በዳዩንም፦ “ለምን ባልንጀራህን ትመታዋለህ?” አለው።

Ver Capítulo



ዘፀአት 2:13
3 Referencias Cruzadas  

እር​ሱም፥ “እኔ ዕብ​ራዊ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ ነኝ፤ ባሕ​ሩ​ንና የብ​ሱን የፈ​ጠ​ረ​ውን የሰ​ማ​ይን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ል​ካ​ለሁ” አላ​ቸው።