La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 12:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይህች ሌሊት ከግ​ብፅ ምድር ስላ​ወ​ጣ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ጠ​በ​ቀች ናት፤ ይህች ሌሊት በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ዘንድ እስከ ልጅ ልጃ​ቸው ድረስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ጠ​በ​ቀች ናት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር በዚያች ሌሊት እነርሱን ከግብጽ ለማውጣት ዘብ የቆመበት በመሆኑ፣ ለሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ እግዚአብሔርን ያከብሩ ዘንድ፣ በዚያች ሌሊት እስራኤላውያን ሁሉ ዘብ መቆም ይኖርባቸዋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከግብጽ ምድር ስላወጣቸው ለጌታ የተጠበቀች ሌሊት ናት፤ ይህች ሌሊት በእስራኤል ልጆች ሁሉ ዘንድ በትውልዳቸው ሁሉ ለጌታ የተጠበቀች ናት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ሕዝቡን እየጠበቀ ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ዕለት ጊዜው ሌሊት ነበር፤ ያም ሌሊት እስራኤላውያን በመጠባበቅ ተግተው የሚያድሩበት ለሚመጣው ትውልድ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሌሊት ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይህች ሌሊት ከግብፅ ምድር ስላወጣቸው ለእግዚአብሔር የተጠበቀች ናት፤ ይህች ሌሊት በእስራኤል ልጆች ሁሉ ዘንድ እስከ ልጅ ልጃቸው ድረስ ለእግዚአብሔር የተጠበቀች ናት።

Ver Capítulo



ዘፀአት 12:42
6 Referencias Cruzadas  

ይህም ቀን መታ​ሰ​ቢያ ይሁ​ና​ችሁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዓል ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም ሥር​ዐት ሆኖ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ።


ከቀን ወደ ቀን በየ​ጊ​ዜው ይህን ሕግ ጠብ​ቁት።


ሙሴም ሕዝ​ቡን አለ፥ “ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ የወ​ጣ​ች​ሁ​ባ​ትን ይህ​ችን ቀን ዐስቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚህ ቦታ በበ​ረ​ታች እጅ አው​ጥ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና። ስለ​ዚህ የቦካ እን​ጀራ አት​ብሉ።


“የቂ​ጣ​ውን በዓል ትጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለህ። በሚ​ያ​ዝያ ወር ከግ​ብፅ ወጥ​ተ​ሃ​ልና በታ​ዘ​ዘው ዘመን በሚ​ያ​ዝያ ወር እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ።