ኤፌሶን 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ አትምሰሉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እንዲህ ካሉ ጋራ አትተባበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ እንዲህ ካሉ ጋር አትተባበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ከእነዚህ ከማይታዘዙ ሰዎች ጋር አትተባበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ከእነርሱ ጋር ተካፋዮች አትሁኑ፤ |
ማኅበሩንም፥ “ከእነዚህ ክፉዎች ሰዎች ድንኳን ፈቀቅ በሉ፤ በኀጢአታቸውም ሁሉ እንዳትጠፉ ለእነርሱ የሆነውን ሁሉ አትንኩ” ብሎ ተናገራቸው።
ተጠራጣሪዎች አትሁኑ፤ ወደማያምኑ ሰዎች አንድነትም አትሂዱ፤ ጽድቅን ከኀጢአት ጋር አንድ የሚያደርጋት ማን ነው? ብርሃንንስ ከጨለማ ጋር የሚቀላቅል ማን ነው?
አሕዛብን ወራሾቹና አካሉ ያደርጋቸው ዘንድ፥ በወንጌልም ትምህርት በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ተስፋ አንድ ይሆኑ ዘንድ።