ያን ጊዜም አዳም አለ፥ “ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፤ ሥጋዋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከባልዋ ተገኝታለችና ሚስት ትሁነኝ።”
ኤፌሶን 5:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቶ ሥጋውን መጥላት የሚቻለው የለም፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ መገባት መግቡ፤ ጠብቁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ማንም የለም፤ ይመግበዋል፤ ይንከባከበዋል፤ ክርስቶስም ለቤተ ክርስቲያን ያደረገው ልክ እንደዚሁ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም የራሱን እካል የሚጠላ ከቶ የለምና፤ ይመግበዋል፤ ይንከባከበውማል። ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ያደረገው እንዲህ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የገዛ ራሱን አካል የሚጠላ ማንም የለም፤ ይልቅስ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን እንደሚያደርገው ዐይነት ራሱን ይመግባል፤ ይንከባከባልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና፥ ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን፥ ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት፥ ይመግበዋል ይከባከበውማል። |
ያን ጊዜም አዳም አለ፥ “ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፤ ሥጋዋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከባልዋ ተገኝታለችና ሚስት ትሁነኝ።”
የምድረ በዳ ዛፍም ፍሬውን ይሰጣል፤ ምድርም ቡቃያዋን ትሰጣለች፤ በምድራቸውም በሰላም ታምነው ይኖራሉ፤ የቀንበራቸውንም ማነቆ በሰበርሁ ጊዜ፥ ከሚገዙአቸውም እጅ ባዳንኋቸው ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
“ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።
ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፤ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?