ኤፌሶን 5:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስውር የሚሠሩት ሥራ ለመናገር የሚያሳፍር ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በድብቅ የሚሠሩትን ነገር መናገር ራሱ አሳፋሪ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳን ያስነውራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጨለማ የሚኖሩ ሰዎች በስውር ስለሚያደርጉት ነገር መናገር እንኳ ያሳፍራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤ |
ሰው በስውር ቦታ ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል እግዚአብሔር።
ይህም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እኔ በወንጌል እንዳስተማርሁ ሰዎችን በልቡናቸው የሰወሩትንና የሸሸጉትን በሚመረምርበት ጊዜ የሚናገሩትና የሚመልሱት እንደሌለ ስለሚያውቁ ነው።
የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።
ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ፤ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ።