በከተማ ከሚኖሩ ዐሥር ገዢዎች ይልቅ ጥበብ ጠቢብን ትረዳዋለች።
በአንድ ከተማ ካሉ ዐሥር ገዦች ይልቅ፣ ጥበብ ጠቢቡን ሰው ኀያል ታደርገዋለች።
በከተማ ከሚኖሩ ከዐሥር ገዢዎች ይልቅ ጥበብ ጠቢብን ታበረታለች።
በአንዲት ከተማ ከሚኖሩ ከዐሥር ገዥዎች ይበልጥ ጥበብ ለአስተዋይ ሰው ብርታትን ትሰጠዋለች።
በከተማ ከሚኖሩ ከአሥር ገዢዎች ይልቅ ጥበብ ጠቢብን ታበረታለች።
ጠቢብ የጸናች ከተማን ይገባባታል፥ ክፉዎች የሚተማመኑበትንም ኀይል ያፈርሳል።
ጠቢብ ሰው ከብርቱ ይሻላል፥ ከታላቅ ርስትም ይልቅ ዕውቀት ያለው ይበልጣል።
ምክርና ሥልጣን የእኔ ናቸው፤ ማስተዋል የእኔ ነው፥ ብርታትም የእኔ ነው።
ድሃና ጠቢብ ብላቴና ከእንግዲህ ወዲህ ተግሣጽን መቀበል ከማያውቅ ከሰነፍ ሽማግሌ ንጉሥ ይሻላል።
የጥበብ ጥላ ከብር ጥላ ይሻላል፤ የጥበብንም ዕውቀት ማብዛት ገንዘብ ላደረጋት ሕይወትን ትሰጠዋለች።