መክብብ 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም እስከ ዛሬ በሕይወት ካሉት ሕያዋን ይልቅ በቀድሞ ዘመን የሞቱትን አመሰገንኋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም የቀድሞ ሙታን፣ ዛሬ በሕይወት ካሉት ሕያዋን ይልቅ፣ ደስተኞች እንደ ሆኑ ተናገርሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም እስከ ዛሬ በሕይወት ካሉት ይልቅ በቀድሞ ዘመን የሞቱትን አመሰገንሁ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እኔ “በዚህ ሁኔታ ላይ በሕይወት ካሉት ይልቅ በቀድሞ ዘመን የሞቱት ይሻላሉ” አልኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም እስከ ዛሬ በሕይወት ካሉት ይልቅ በቀድሞ ዘመን የሞቱትን አመሰገንሁ፥ |
ከእንግዲህ ወዲህ አይመለስምና፥ የተወለደባትንም ሀገር አያይምና ለሚወጣ እጅግ አልቅሱ እንጂ ለሞተ አታልቅሱ፤ አትዘኑለትም።