ሣቅን፥ “ሽንገላ ነህ፤ ደስታንም፦ ምን ታደርጋለህ?” አልሁት።
ደግሞም፣ “ሣቅ ሞኝነት ነው፤ ተድላስ ምን ይጠቅማል?” አልሁ።
“ሳቅን፦ ዕብደት፥ ደስታንም፦ ዋጋ ቢስ” አልሁት።
ሳቅ ከሞኝነት ያልተሻለ፥ ተድላ ደስታም ዋጋ የሌለው ነገር መሆኑን አስተዋልኩ።
ሳቅን፦ ዕብድ ነህ፥ ደስታንም፦ ምን ታደርጋለህ? አልሁት።
ከደስታ ጋር ኀዘን አይቀላቀልም፥ የደስታ ፍጻሜ ግን ወደ ኀዘን ይመለሳል።
ደስ ያላት ልብ ፈውስን ታገኛለች፤ ኀዘንተኛ ሰው ግን አጥንቱን ያደርቃል።