La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መክብብ 2:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጠቢብ ወይም አላ​ዋቂ እን​ደ​ሚ​ሆን ከፀ​ሐይ በታ​ችም በደ​ከ​ም​ሁ​በ​ትና ጠቢብ በሆ​ን​ሁ​በት በድ​ካሜ ሁሉ ይሰ​ለ​ጥን እንደ ሆነ የሚ​ያ​ውቅ ሰው ማን ነው? ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱ ጠቢብ ወይም ሞኝ ይሆን እንደ ሆነ ማን ያውቃል? ሆኖም ከፀሓይ በታች ድካሜንና ችሎታዬን ባፈሰስሁበት ሥራ ሁሉ ላይ ባለቤት ይሆንበታል፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጠቢብ ወይም አላዋቂ እንደሚሆን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? ከፀሐይ በታች በደከምሁበትና ጠቢብ በሆንሁበት በድካሜ ሁሉ ላይ ይሠለጥንበታል፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከእኔ በኋላ የሚመጣው ጠቢብ ይሁን ሞኝ ተለይቶ አይታወቅም፤ ይሁን እንጂ እኔ የደከምኩበትንና በጥበቤ ያተረፍኩትን ነገር ሁሉ ወስዶ ባለቤት ይሆናል፤ ይህም ከንቱ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጠቢብ ወይም ሰነፍ እንዲሆን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? ከፀሐይ በታች በደከምሁበትና ጠቢብ በሆንሁበት በድካሜ ሁሉ ላይ ጌታ ይሆንበታል፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

Ver Capítulo



መክብብ 2:19
14 Referencias Cruzadas  

ሰሎ​ሞ​ንም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፥ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ተቀ​በረ፤ ልጁም ሮብ​ዓም በፋ​ን​ታው ነገሠ።


ንጉ​ሡም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች የመ​ከ​ሩ​ትን ምክር ትቶ ለሕ​ዝቡ ጽኑ ምላሽ መለ​ሰ​ላ​ቸው።


እጄ የሠ​ራ​ቻ​ትን ሥራ​ዬን ሁሉ፥ የደ​ከ​ም​ሁ​በ​ት​ንም ድካ​ሜን ሁሉ ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነበረ፥ ከፀ​ሐይ በታ​ችም ትርፍ አል​ነ​በ​ረም።


እኔም ተመ​ልሼ ልቤን ከፀ​ሐይ በታች በደ​ከ​ም​ሁ​በት ድካም ሁሉ ተስፋ አስ​ቈ​ረ​ጥ​ሁት።


ያም ዕድል ፋን​ታው ነውና ሰው በሥ​ራው ደስ ከሚ​ለው በቀር ሌላ መል​ካም ነገር እን​ደ​ሌ​ለው አየሁ፤ ከእ​ርሱ በኋ​ላስ የሚ​ሆ​ነ​ውን ያይ ዘንድ የሚ​ያ​መ​ጣው ማን ነው?


ከፀ​ሓይ በታ​ችም ጥበ​ብን አየሁ፥ እር​ስ​ዋም በእኔ ዘንድ ታላቅ ናት።


ጌታ​ውም ዐመ​ፀ​ኛ​ውን መጋቢ እንደ ብልህ ሰው ስለ ሠራ አመ​ሰ​ገ​ነው፤ ከብ​ር​ሃን ልጆች ይልቅ የዚህ ዓለም ልጆች በዓ​ለ​ማ​ቸው ይራ​ቀ​ቃ​ሉና።


ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፤ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።


በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፤ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።


ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።