እርሱም አለ፥ “ልጄ ከእናንተ ጋር አይወርድም፤ ወንድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀርቶአልና፤ በምትሄዱበት መንገድ ምናልባት ክፉ ነገር ቢያገኘው ሽምግልናዬን በኀዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።”
መክብብ 12:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፍ ያለውን ተመልክተው ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፤ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፍሬም ሳይበተን፤ ሰው ወደ ዘለዓለም ቤቱ ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳገት መውጣት ሲያርድ፣ መንገድም ሲያስፈራ፣ የአልሙን ዛፍ ሲያብብ፣ አንበጣም ራሱን ሲጐትት፣ ፍላጎት ሲጠፋ፤ በዚያም ጊዜ ሰው ወደ ዘላለማዊ ቤቱ ይሄዳል፤ አልቃሾችም በአደባባዮች ይዞራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፍ ያለውን ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፥ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፈቃድም ሲጠፋ፥ ሰው ወደ ዘለዓለም ቤት ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ከፍተኛ ስፍራዎች መውጣት ያስፈራሃል፤ በእግር መጓዝም አደገኛ ይሆንብሃል፤ ጠጒርህ እንደ ለውዝ አበባ ነጭ ይሆናል፤ ራስህን ችለህ መራመድ አቅቶህ እንደ አሮጌ ኩብኩባ ትጐተታለህ፤ ፍላጎትህ መቀስቀሱ ይቀራል። ድምፅ እንኳ ከእንቅልፍህ ይቀሰቅስሃል። ሰውም ወደ ዘለዓለማዊ መኖሪያው ይሄዳል፤ አልቃሾችም በየመንገዱ እያለቀሱ ይሸኙታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፍ ያለውን ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፥ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፈቃድም ሲጠፋ፥ ሰው ወደ ዘላለም ቤት ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፥ |
እርሱም አለ፥ “ልጄ ከእናንተ ጋር አይወርድም፤ ወንድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀርቶአልና፤ በምትሄዱበት መንገድ ምናልባት ክፉ ነገር ቢያገኘው ሽምግልናዬን በኀዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።”
ይህንም ከእኔ ለይታችሁ ደግሞ ብትወስዱት በመንገድም ክፉ ቢያገኘው፥ እርጅናዬን በኀዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።
ብላቴናው ከእኛ ጋር እንደሌለ በአየ ጊዜ ይሞታል፤ አገልጋዮችህም የአገልጋይህን የአባታችንን እርጅና በኀዘን ወደ መቃብር እናወርዳለን።
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።
እስከ ሽምግልና ድረስ እኔ ነኝ፤ እስከ ሽበትም ድረስ እኔ ነኝ፤ እኔ እታገሣችኋለሁ፤ እኔ ሠርቻለሁ፤ እኔም ይቅር እላለሁ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፤ እኔም አድናችኋለሁ።
እነርሱና አባቶቻቸውም በአላወቋቸው አሕዛብ መካከል እበትናቸዋለሁ፤ እስከ አጠፋቸውም ድረስ በስተ ኋላቸው ሰይፍን እሰድድባቸዋለሁ።
“በሽበታሙ ፊት ተነሣ፤ ሽማግሌውንም አክብር፤ አምላክህን እግዚአብሔርንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።