በሰዎች ስንፍናና ቦዘኔነት የቤት ጣራ ይዘብጣል፥ በእጆች ስንፍናም ቤት ያፈስሳል።
ሰው ሰነፍ ከሆነ ጣራው ይዘብጣል፤ እጆቹም ካልሠሩ ቤቱ ያፈስሳል።
ተግባር በመፍታት ጣራው ይዘብጣል፥ በእጅም መታከት ቤት ያፈስሳል።
ሰው ቤቱን ከመጠገን ቸል ቢል ጣራው ይዘብጣል፤ ክዳኑም ያፈሳል።
የተመረጡ ሰዎች እጅ ፈጥኖ ይገዛል፤ ሐሰተኞች ሰዎች ግን ለምርኮ ይሆናሉ።
ብልሆች ሴቶች ቤቶችን ይሠራሉ፤ ሰነፎች ሴቶች ግን በእጃቸው ያፈርሳሉ።
ታካች ሰው ሲያሽሟጥጡት አያፍርም፤ ስለዚህ በመከር ጊዜ ይለምናል፥ የሚሰጠውም የለም። በክምሩ እያለ ስንዴ የሚበደር እንደዚሁ ነው።
ታካችን ምኞቱ ትገድለዋለች፥ እጆቹ ምንም ይሠሩ ዘንድ አይፈቅዱምና።
ሰካራምና አመንዝራ ይደኸያል፥ እንቅልፋምም ሁሉ የተቦጫጨቀ ጨርቅ ይለብሳል።
ነገር ግን ሁላችሁም በዚች ተስፋችሁ እንዲሁ ትጋታችሁን እስከ መጨረሻው ታሳዩ ዘንድ እንወዳለን።