ለፊተኞቹ ነገሮች መታሰቢያ የላቸውም፤ ለኋለኞቹም ነገሮች ከእነርሱ በኋላ በሚነሡት ሰዎች ዘንድ መታሰቢያ አይገኝላቸውም።
መክብብ 1:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ “ይህ ነገር አዲስ ነው” ብሎ የሚናገር ማን ነው? እርሱ ከእኛ በፊት በነበሩት ዘመናት ተደርጓል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንም፣ “እነሆ፤ ይህ አዲስ ነገር ነው!” ሊል የሚችለው አንዳች ነገር አለን? ቀድሞውኑ በዚሁ የነበረ ነው፤ ከእኛ በፊት የሆነ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም፦ እነሆ፥ ይህ ነገር አዲስ ነው ማለት ይችላልን? እርሱ ከእኛ በፊት በነበሩት ዘመናት ተደርጎአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ሰው “እነሆ ይህ አዲስ ነገር ነው!” ቢል ያ ነገር እኛ ከመወለዳችን አስቀድሞ የነበረ ሆኖ ይገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም፦ እነሆ፥ ይህ ነገር አዲስ ነው ይል ዘንድ ይችላልን? እርሱ ከእኛ በፊት በነበሩት ዘመናት ተደርጎአል። |
ለፊተኞቹ ነገሮች መታሰቢያ የላቸውም፤ ለኋለኞቹም ነገሮች ከእነርሱ በኋላ በሚነሡት ሰዎች ዘንድ መታሰቢያ አይገኝላቸውም።
የሆነው ነገር እርሱ የሚሆን ነው፥ የተደረገውም ነገር እርሱ የሚደረግ ነው፥ ከፀሐይም በታች ከተደረገው ሁሉ አዲስ ነገር የለም።
እኔም ጥበብን፥ ሽንገላንና ስንፍናን አይ ዘንድ ተመለከትሁ ፥ ምክርን የሚከተል፥ ምሳሌንስ ሁሉ የሚያደርግላት ሰው ማን ነው?
“እናንተ አንገታችሁ የደነደነ፥ ልባችሁም የተደፈነ፥ ጆሮአችሁም የደነቈረ፥ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ዘወትር ትቃወማላችሁ።
ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም የተጣሉ ሰዎች ሆነው እውነትን ይቃወማሉ።