ዘዳግም 9:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አሮንን ሊያጠፋው እጅግ ተቈጣው፤ ስለ አሮንም ደግሞ በዚያን ጊዜ ጸለይሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አሮንን ሊያጠፋው ክፉኛ ተቈጥቶ ነበር፤ በዚያ ጊዜ ለአሮንም ጸለይሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ አሮንንም እጅግ ተቆጥቶ ሊያጠፋው ስለ ነበር፥ በዚያን ጊዜ ስለ አሮንም ደግሞ ጸለይሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በአሮንም ላይ እጅግ ስለ ተቈጣ ሊገድለው ተቃርቦ ነበር፤ ስለዚህ በዚያው ጊዜ ለአሮንም ጭምር ጸለይኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም አሮንን ሊያጠፋው እጅግ ተቆጣው፤ ስለ አሮንም ደግሞ በዚያን ጊዜ ጸለይሁ። |
እግዚአብሔርም ሊያጠፋችሁ ከተቈጣባችሁ ከቍጣውና ከመዓቱ የተነሣ ፈራሁ፤ እግዚአብሔርም በዚያን ጊዜ ደግሞ ሰማኝ።
ስለ አደረጋችሁትም ኀጢአት የጥጃውን ምስል ወሰድሁ፤ በእሳትም አቃጠልሁት፤ አደቀቅሁትም፤ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨሁት፤ እንደ ትቢያም ሆነ፤ ትቢያውንም ከተራራው በሚወርድ ወንዝ ጨመርሁት።