እንደማዝዝህ የምታደርገውን ሁሉ ታውቅ ዘንድ፥ በሙሴ ሕግ የተጻፈውን ሥርዐቱንና ትእዛዛቱን፥ ፍርዱንና ምስክሩንም ትጠብቅ ዘንድ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቅ።
ዘዳግም 4:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከግብፅ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእስራኤል ልጆች የተናገረው ምስክርና ሥርዐት፤ ፍርድም ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከግብጽ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ምስክርነቶች፣ ሥርዐቶችና ሕጎች እነዚህ ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግብጽ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእስራኤል ልጆች የተናገረው ምስክርና ሥርዓት፥ ሕጎችም እነዚህ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከግብጽ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእስራኤላውያን ያስተላለፈላቸው ድንጋጌዎች፥ ሕጎችና ደንቦች ከዚህ በላይ ያሉት ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴና የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ከወጡ በኋላ በመቱት፥ በሐሴቦን ተቀምጦ በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ምድር፥ በቤተ ፌጎር አንጻር ባለው ሸለቆ በዮርዳኖስ ማዶ፥ ከግብፅ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእስራኤል ልጆች የተናገረው ምስክርና ሥርዓት ፍርድም ይህ ነው። |
እንደማዝዝህ የምታደርገውን ሁሉ ታውቅ ዘንድ፥ በሙሴ ሕግ የተጻፈውን ሥርዐቱንና ትእዛዛቱን፥ ፍርዱንና ምስክሩንም ትጠብቅ ዘንድ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቅ።
“አሁንም እስራኤል ሆይ፥ እንድታደርጉአቸው፥ በሕይወትም እንድትኖሩ፥ እንድትበዙም፥ የአባቶቻችሁም አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ ዛሬ የማስተምራችሁን ሥርዐትና ፍርድ ስሙ።
ሙሴና የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ከወጡ በኋላ በመቱት፥ በሐሴቦን ተቀምጦ በነበረው በአሞሬዎን ንጉሥ በሴዎን ምድር፥ በቤተ ፌጎር አቅራቢያ ባለው ሸለቆ በዮርዳኖስ ማዶ፤