ዘዳግም 4:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትወርሱአት ዘንድ ተሻግራችሁ በምትገቡባት ምድር የምታደርጉአትን ሥርዐትና ፍርድ አስተምራችሁ ዘንድ እግዚአብሔር በዚያን ጊዜ አዘዘኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ውስጥ የምትከተሏቸውን ሥርዐትና ሕግ እንዳስተምራችሁ በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር አዘዘኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትወርሱአት ዘንድ ተሻግራችሁ በምትገቡባት ምድር የምታደርጉትን ሥርዓትና ሕግጋት እንዳስተምራችሁ ጌታ በዚያን ጊዜ አዘዘኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም፥ ድል አድርጋችሁ በምትወርሱአት ምድር ስትኖሩ ልትፈጽሙት የሚገባውን ሕግና ሥርዓት ሁሉ እንዳስተምራችሁ እግዚአብሔር አዞኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትወርሱአት ዘንድ ተሻግራችሁ በምትገቡባት ምድር የምታደርጉአትን ሥርዓትና ፍርድ አስተምራችሁ ዘንድ እግዚአብሔር በዚያን ጊዜ አዘዘኝ። |
“በሕይወት ትኖሩ ዘንድ፥ ትበዙም ዘንድ፥ ትወርሱአትም ዘንድ ዮርዳኖስን የምትሻገሩላትን ምድር እንድትወርሷት ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ፤
“እግዚአብሔር በኮሬብ ተራራ በእሳት መካከል ሆኖ በተናገራችሁ ቀን መልኩን ከቶ አላያችሁምና ሰውነታችሁን እጅግ ጠብቁ፤
ዛሬ እኔ ያዘዝኋችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትጠብቃላችሁ እንጂ ባዘዝኋችሁ ቃል ላይ አትጨምሩም፤ ከእርሱም አታጐድሉም።