እኔም፦ ከእናንተ እያንዳንዱ ርኵሰቱን ከፊቱ ያስወግድ፤ በግብፅም ጣዖታት አትርከሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ አልኋቸው።
ዘዳግም 29:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን እኛ በግብፅ ምድር እንደ ተቀመጥን በመካከላቸውም ባለፋችሁባቸው አሕዛብ መካከል እንዳለፍን ዐውቃችኋልና፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በግብጽ ምድር እንዴት እንደ ኖርንና ወደዚህ ስንመጣም በየአገሮቹ ውስጥ እንዴት እንዳለፍን ራሳችሁ ታውቃላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በግብጽ ምድር እንዴት እንደ ኖርንና ወደዚህ ስንመጣም በየአገሮቹ ውስጥ እንዴት እንዳለፍን ራሳችሁ ታውቃላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በግብጽ ምድር እንዴት እንደ ኖርንና ባለፋችሁባቸውም ሕዝቦች መካከል እንዴት እንደ መጣን ታውቃላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እኛ በግብፅ ምድር እንደ ተቀመጥን በመካከላቸውም ባለፋችሁባቸው አሕዛብ መካከል እንዳለፍን አውቃችኋልና፥ |
እኔም፦ ከእናንተ እያንዳንዱ ርኵሰቱን ከፊቱ ያስወግድ፤ በግብፅም ጣዖታት አትርከሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ አልኋቸው።
ለሎጥም ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከአሞን ልጆች ምድር ርስት አልሰጥህምና በአሞን ልጆች አቅራቢያ ስትደርስ አትጣላቸው፤ አትውጋቸውም።’
ደግሞም አለ፦ ተነሥታችሁ ሂዱ፤ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፤ እነሆ፥ አሞሬዎናዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንን፥ ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ እርስዋን ግዛት፤ ውረሳት፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ።
ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ በሴይር ላይ በተቀመጡት በወንድሞቻችሁ በዔሳው ልጆች ሀገር ታልፋላችሁ፤ እነርሱ ይፈሩአችኋል፤ እንግዲህ እጅግ ተጠንቀቁ።
“እግዚአብሔርም አለኝ፦ እኔ አሮኤርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድሩ ርስት አልሰጣችሁምና ሞዓባውያንን አትጣላ፤ በሰልፍም አትውጋቸው።
ነገር ግን ዛሬ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ከእኛ ጋር በዚህ ከሚቆም ሰው ጋር፥ ዛሬም ከእኛ ጋር በዚህ ከሌለ ሰው ጋር ነው እንጂ፤
ርኩስነታቸውንም፥ በእነርሱም ዘንድ የነበሩትን የእንጨትና የድንጋይ፥ የብርና የወርቅም ጣዖቶቻቸውን አይታችኋልና፥