መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፤ ምስፍናም ከአብራኩ፥ ለእርሱ የሚጠብቀውን እስኪያገኝ ድረስ፤ የአሕዛብ ተስፋቸው እርሱ ነውና፤
ዘዳግም 28:57 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአካልዋ የሚወጣውን የእንግዴ ልጅ፥ የምትወልዳቸውንም ልጆች፤ በደጆችህ ውስጥ ጠላቶችህ፤ ከብበው ባስጨነቁህና መከራ ባሳዩህ ጊዜ ሁሉን ስላጣች በስውር ትበላቸዋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከማሕፀኗ የወጣውን እንግዴ ልጇንና የምትወልዳቸውን ሕፃናት ትጠየፋለች፤ ይህን የምታደርገውም በመከራው ወቅት ጠላቶችህ ከተሞችህን ከብበው በሚያስጨንቁህ ጊዜ፣ እነርሱን ደብቃ ለመብላት ስትል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከማሕፀኗ የወጣውን እንግዴ ልጅንና የምትወልዳቸውን ልጆች ትጠየፋለች፤ ይህን የምታደርገውም በመከራው ወቅት ጠላቶችህ ከተሞችህን ከበው በሚያስጨንቁህ ጊዜ እነርሱን ተደብቃ ለመብላት ስትል ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያ ተስፋ በሚያስቈርጠው፥ በከተሞችህ ሁሉ ላይ በሚደረገው የጠላት ከበባ ወቅት ሌላ ምንም የሚበላ ነገር ስለሌላት በምሥጢር ከምትበላቸው ከማሕፀንዋ ከወጡ ልጆችዋና ከእንግዴልጅዋ ለማንም አትሰጥም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በወንድና በሴት ልጅዋም፥ በእግርዋ መካከል በሚወጣው በእንግዴ ልጅ፥ በምትወልዳቸውም ልጆች ትቀናለች፤ በደጆችህም ውስጥ ጠላቶችህ ከብበው ባስጨነቁህና መከራ ባሳዩህ ጊዜ ሁሉን ስላጣች በስውር ትበላቸዋለች። |
መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፤ ምስፍናም ከአብራኩ፥ ለእርሱ የሚጠብቀውን እስኪያገኝ ድረስ፤ የአሕዛብ ተስፋቸው እርሱ ነውና፤
ንጉሡም፥ “ምን ሆነሻል?” አላት፤ እርስዋም፥ “ይህች ሴት፦ ዛሬ እንድንበላው ልጅሽን አምጪ፤ ነገም ልጄን እንበላለን አለችኝ።
ልጄንም ቀቅለን በላነው፤ በማግሥቱም፦ እንድንበላው ልጅሽን አምጪ አልኋት፤ ልጅዋንም ሸሸገችው” ብላ መለሰችለት።
“በውኑ ሴት፥ ልጅዋን ትረሳለችን? ከማኅፀንዋ ለተወለደውስ አትራራምን? ሴት ይህን ብትረሳ፥ እኔ አንቺን አልረሳሽም።
ጠላቶችህም በሀገርህ ውስጥ ከብበው ባስጨነቁህና መከራ ባሳዩህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር የሚሰጥህን የሆድህን ፍሬ፥ የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ።