ሄ። ስለ ኀጢአቷ ብዛት እግዚአብሔር አዋርዶአታልና የሚዘባበቱባት በራስዋ ላይ ሆኑ፤ ጠላቶችዋም ተደሰቱ፤ ሕፃናቶችዋም በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል።
ዘዳግም 28:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ያበድርሃል፤ አንተ ግን አታበድረውም፤ እርሱ ራስ ይሆናል፤ አንተም ጅራት ትሆናለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ያበድርሃል እንጂ አንተ አታበድረውም። እርሱ ራስ ይሆናል፤ አንተ ግን ጅራት ትሆናለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ያበድርሃል፤ አንተም ትበደረዋለህ። እርሱ ራስ ይሆናል፤ አንተ ግን ጅራት ትሆናለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መጻተኞች ለአንተ ገንዘብ አበዳሪዎች ይሆናሉ፤ አንተ ግን ለእነርሱ የምታበድራቸው ገንዘብ አይኖርህም፤ በመጨረሻም እነርሱ እንደ ራስ መሪ ይሆናሉ፤ አንተ ግን እንደ ጅራት ወደ ኋላ ትቀራለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ያበድርሃል፥ አንተ ግን አታበድረውም፤ እርሱ ራስ ይሆናል፥ አንተም ጅራት ትሆናለህ። |
ሄ። ስለ ኀጢአቷ ብዛት እግዚአብሔር አዋርዶአታልና የሚዘባበቱባት በራስዋ ላይ ሆኑ፤ ጠላቶችዋም ተደሰቱ፤ ሕፃናቶችዋም በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል።
ፌ። እግዚአብሔር ያሰበውን አደረገ፤ በቀድሞ ዘመን ያዘዘውንም ቃል ፈጸመ፤ አፈረሳት፤ አልራራላትምም፤ ጠላትንም ደስ አሰኘብሽ፤ የጠላቶችሽንም ቀንድ ከፍ ከፍ አደረገ።