ኢየሩሳሌምንም አጠፋት፥ አለቆቹንም ሁሉ፥ ጽኑዓኑንና ኀያላኑን ሁሉ፥ ጠራቢዎቹንም ሁሉ፥ ብረት ሠራተኞቹንም ሁሉ ዐሥር ሺህ ምርኮኞችን ሁሉ አፈለሰ፤ ከሀገሩ ድሆች በቀር ማንም አልቀረም።
ዘዳግም 28:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ትወልዳለህ፤ ማርከው ይወስዷቸዋልና አይቀሩልህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ትወልዳለህ፤ ነገር ግን በምርኮ ስለሚወሰዱ፣ ዐብረውህ አይኖሩም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንዶችና ሴቶች ልጆች ትወልዳለህ፤ ነገር ግን በምርኮ ስለሚወሰዱ ያንተ አሆኑም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ትወልዳለህ፤ ነገር ግን የጦር ምርኮኞች ሆነው ስለሚወሰዱ ታጣቸዋለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንዶችና ሴቶች ልጆች ይወለዱልሃል፤ በምርኮም ይሄዳሉና ለአንተ አይሆኑልህም። |
ኢየሩሳሌምንም አጠፋት፥ አለቆቹንም ሁሉ፥ ጽኑዓኑንና ኀያላኑን ሁሉ፥ ጠራቢዎቹንም ሁሉ፥ ብረት ሠራተኞቹንም ሁሉ ዐሥር ሺህ ምርኮኞችን ሁሉ አፈለሰ፤ ከሀገሩ ድሆች በቀር ማንም አልቀረም።
የእስራኤል ልጆች ከወንድሞቻቸው ሦስት መቶ ሺህ ሴቶችን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ማረኩ፤ እጅግም ምርኮ ከእነርሱ ወስደው ወደ ሰማርያ አገቡ።
ጻዴ። ቃሉን አማርሬአለሁና እግዚአብሔር ጻድቅ ነው። እናንተ አሕዛብ ሁሉ እባካችሁ ስሙ፤ መከራዬንም ተመልከቱ፤ ደናግሎችና ጐልማሶች ተማርከው ሄደዋልና።
ሄ። ስለ ኀጢአቷ ብዛት እግዚአብሔር አዋርዶአታልና የሚዘባበቱባት በራስዋ ላይ ሆኑ፤ ጠላቶችዋም ተደሰቱ፤ ሕፃናቶችዋም በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል።
ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ለሌላ ሕዝብ ይሰጣሉ፤ ራሳቸውንም ሲመቱአቸው በዐይኖችህ ታያለህ፤ ልታደርገውም የምትችለው የለም።