ዘዳግም 28:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሬህ በፊትህ ይታረዳል፤ ከእርሱም አትበላም። አህያህ ከእጅህ በግድ ይወሰዳል፤ ወደ አንተም አይመለስም፤ በጎችህ ለጠላቶችህ ይሰጣሉ፤ የሚረዳህም አታገኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሬህ ዐይንህ እያየ ይታረዳል፤ ከሥጋውም አንዳች አትቀምስም። አህያህም በግድ ይወሰድብሃል፤ አይመለስልህም። በጎችህ ለጠላቶችህ ይሰጣሉ፤ የሚያስጥላቸውም አይኖርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሬህ ዐይንህ እያየ ይታረዳል፤ አንዳች ግን አትቀምሰውም። አህያህም በግድ ይወሰድብሃል፤ ለአንተም አይመለስልህም። በጎችህ ለጠላቶችህ ይሰጣሉ፤ የሚረዳህ ማንም አይኖርም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብትህ በፊትህ፥ ዐይንህ እያየ ይታረዳል፤ ነገር ግን ከሥጋው አትቀምስም፤ አህዮችህ በፊትህ ተስበው ይወሰዳሉ፤ ነገር ግን አይመለሱልህም፤ በጎችህ ለጠላቶችህ ተላልፈው ይሰጣሉ፤ እነርሱን ለማዳን የሚረዳህም የለም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሬህ በፊትህ ይታረዳል፥ ከእርሱም አትበላም፤ አህያህ ከእጅህ በግድ ይወሰዳል፥ ወደ አንተም አይመለስም፤ በግህ ለጠላቶችህ ትሰጣለች፥ የሚያድንህም አታገኝም። |
እግዚአብሔር፥ “ከእንግዲህ ወዲህ በእርግጥ ለጠላቶችሽ መብል ይሆን ዘንድ እህልሽን አልሰጥም፥ መጻተኞችም የደከምሽበትን ወይንሽን አይጠጡም፤” ብሎ በጌትነቱና በክንዱ ኀይል ምሎአል።
መከርህንና እንጀራህን ይበላሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህንም ይበሉአቸዋል፤ በጎችህንና ላሞችህንም ይበላሉ፤ ወይንህንና በለስህንም፥ ዘይትህንም ይበላሉ፤ የምትታመናቸውን የተመሸጉ ከተሞችህንም በሰይፍ ያጠፋሉ።”
ሚስት ታገባለህ፤ ሌላም ሰው ይነጥቅሃል፤ ቤት ትሠራለህ፤ በእርሱም አትቀመጥበትም፤ ወይን ትተክላለህ፤ ከእርሱም አትለቅምም።
ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ለሌላ ሕዝብ ይሰጣሉ፤ ራሳቸውንም ሲመቱአቸው በዐይኖችህ ታያለህ፤ ልታደርገውም የምትችለው የለም።
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግዚአብሔርም በምድያም እጅ ሰባት ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው።
በእነርሱም ላይ ይሰፍሩ ነበር፤ ወደ ጋዛም እስከሚደርሱ የእርሻቸውን ፍሬ ያጠፉ ነበር፤ በእስራኤልም ምድር ለሕይወት የሚሆን ምንም አይተዉም ነበር፤ ከመንጋዎችም በሬ ወይም አህያ ቢሆን አይተዉም ነበር።