ዘዳግም 28:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛሬም ካዘዝሁህ ከእነዚህ ቃሎች ወደ ቀኝ፥ ወደ ግራም ፈቀቅ ባትል፥ ታመልካቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት ባትከተል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌሎችን አማልክት በመከተል እነርሱን በማገልገል ዛሬ ከምሰጥህ ትእዛዞች ቀኝም ግራም አትበል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌሎችን አማልክት በመከተል እነርሱን በማገልገል ዛሬ ከምሰጥህ ትእዛዞች ቀኝም ግራም አትበል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማናቸውም ሁኔታ ከእነዚህ ትእዛዞች በመውጣት ለባዕዳን አማልክት መስገድና እነርሱን ማገልገል አይገባህም። |
ልባችሁ እንዳይስት፥ ፈቀቅ እንዳትሉ፥ ሌሎችንም አማልክት እንዳታመልኩ፥ እንዳትሰግዱላቸውም ተጠንቀቁ።
አገልጋዬ ሙሴ እንደ አዘዘህ ሕግን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ ጽና፤ እጅግም በርታ፤ ሁሉን እንዴት እንደምትሠራ ታውቅ ዘንድ ከእርሱ ወደ ቀኝ ወደ ግራም አትበል።