ዘዳግም 24:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህ እግዚአብሔር ከግብፅ ባወጣችሁ ጊዜ በመንገድ ሳላችሁ በማርያም ላይ ያደረገውን ዐስብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከግብጽ ከወጣችሁ በኋላ በመንገድ ላይ ሳላችሁ አምላክህ እግዚአብሔር በማርያም ላይ ያደረገባትን አስታውሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግብጽ ከወጣችሁ በኋላ በመንገድ ላይ ሳላችሁ ጌታ እግዚአብሔር በማርያም ላይ ያደረገባትን አስታውሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከግብጽ ወጥታችሁ በጒዞ ላይ ሳላችሁ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር በማርያም ላይ ያደረገውን አስታውሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ በመንገድ ሳላችሁ በማርያም ላይ ያደረገውን አስብ። |
“የእስራኤል ልጆች ለምጻሙን ሁሉ ፈሳሽ ነገርም ያለበትን ሁሉ በሰውነቱ የረከሰውን ሁሉ ከሰፈሩ እንዲያወጡ እዘዛቸው፤