የወይንህን ቃርሚያ አጥርተህ አትቃርም፤ የወደቀውንም የወይንህን ፍሬ አትሰብስብ፤ ለድሆችና ለእንግዶች ተወው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።
ዘዳግም 24:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወይራህን ፍሬ በለቀምህ ጊዜ ከቅርንጫፎቹ ላይ አጥርተህ ለመልቀም ዳግመኛ አትመለስ፤ ለመጻተኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመበለትም ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወይራ ዛፍህን ፍሬ በምታራግፍበት ጊዜ፣ በየቅርንጫፉ ላይ የቀረውን ለመቃረም ተመልሰህ አትሂድ፤ ለመጻተኛው፣ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወይራ ዛፍህን ፍሬ በምታራግፍበት ጊዜ በየቅርንጫፉላይ የቀረውን ለመቃረም ተመልሰህ አትሂድ፤ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይራ ዛፍ ፍሬህንም አንድ ጊዜ ከለቀምክ በኋላ የቀረውን ፍሬ ለመውሰድ እንደገና ወደ እርሱ አትመለስ፤ እርሱን ለመጻተኞች፥ ወላጆቻቸው ለሞቱባቸው ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ተውላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወይራህን ፍሬ ባረገፍህ ጊዜ ከቅርንጫፎቹ ላይ ማርገፉን ለማጣራት አትመለስ፤ ለመጻተኛና ለድሀ አደግ ለመበለትም ይሁን። |
የወይንህን ቃርሚያ አጥርተህ አትቃርም፤ የወደቀውንም የወይንህን ፍሬ አትሰብስብ፤ ለድሆችና ለእንግዶች ተወው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።
“የምድራችሁንም መከር በሰበሰባችሁ ጊዜ የእርሻችሁን አጨዳ አታጥሩ፤ ስታጭዱም የወደቀውን ቃርሚያ አትልቀሙ።
“የእርሻህን መከር ባጨድህ ጊዜ ነዶም ረስተህ በእርሻህ ብታስቀር፥ ትወስደው ዘንድ አትመለስ፤ አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ፥ ለመጻተኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመበለትም ተወው።