ዘዳግም 24:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 የወይራ ዛፍህን ፍሬ በምታራግፍበት ጊዜ በየቅርንጫፉላይ የቀረውን ለመቃረም ተመልሰህ አትሂድ፤ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 የወይራ ዛፍህን ፍሬ በምታራግፍበት ጊዜ፣ በየቅርንጫፉ ላይ የቀረውን ለመቃረም ተመልሰህ አትሂድ፤ ለመጻተኛው፣ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 የወይራ ዛፍ ፍሬህንም አንድ ጊዜ ከለቀምክ በኋላ የቀረውን ፍሬ ለመውሰድ እንደገና ወደ እርሱ አትመለስ፤ እርሱን ለመጻተኞች፥ ወላጆቻቸው ለሞቱባቸው ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ተውላቸው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 የወይራህን ፍሬ በለቀምህ ጊዜ ከቅርንጫፎቹ ላይ አጥርተህ ለመልቀም ዳግመኛ አትመለስ፤ ለመጻተኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመበለትም ይሁን። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 የወይራህን ፍሬ ባረገፍህ ጊዜ ከቅርንጫፎቹ ላይ ማርገፉን ለማጣራት አትመለስ፤ ለመጻተኛና ለድሀ አደግ ለመበለትም ይሁን። Ver Capítulo |