La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 24:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“አባ​ቶች ስለ ልጆ​ቻ​ቸው አይ​ገ​ደሉ፤ ልጆ​ችም ስለ አባ​ቶ​ቻ​ቸው አይ​ገ​ደሉ፤ ነገር ግን ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ በኀ​ጢ​አቱ ይገ​ደል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አባቶች በልጆቻቸው፣ ልጆችም በአባቶቻቸው አይገደሉ፤ እያንዳንዱ በራሱ ኀጢአት ይገደል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“አባቶች ስለ ልጆች አይገደሉ፥ ልጆችም ስለ አባቶች አይገደሉ፥ ነገር ግን ሁሉ እያንዳንዱ በኃጢአቱ ይገደል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ልጆቻቸው በሠሩት ወንጀል ወላጆች በሞት መቀጣት የለባቸውም፤ ወላጆችም በፈጸሙት ወንጀል ልጆቻቸው በሞት አይቀጡ፤ እያንዳንዱ ሰው በሠራው ወንጀል በሞት ይቀጣ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አባቶች ስለ ልጆች አይገደሉ፥ ልጆችም ስለ አባቶች አይገደሉ፤ ነገር ግን ሁሉ እያንዳንዱ በኃጢአቱ ይገደል።

Ver Capítulo



ዘዳግም 24:16
8 Referencias Cruzadas  

እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ቃል ኪዳን እንደ ተጻፈ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሰው ሁሉ በገዛ ኀጢ​አቱ ይሙት እንጂ አባ​ቶች በል​ጆ​ቻ​ቸው፥ ልጆ​ችም በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ፋንታ አይ​ሙቱ” ብሎ እን​ዳ​ዘዘ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ግን አል​ገ​ደ​ለም።


ኀጢ​አ​ትን የም​ት​ሠራ ነፍስ እር​ስዋ ትሞ​ታ​ለች፤ ልጅ የአ​ባ​ቱን ኀጢ​አት አይ​ሸ​ከ​ምም፤ አባ​ትም የል​ጁን ኀጢ​አት አይ​ሸ​ከ​ምም፤ የጻ​ድቁ ጽድቅ በራሱ ላይ ይሆ​ናል፤ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ኀጢ​አት በራሱ ላይ ይሆ​ናል።


እነሆ ነፍ​ሳት ሁሉ የእኔ ናቸው፤ የአ​ባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች እን​ዲሁ የልጅ ነፍስ የእኔ ናት፤ ኀጢ​አት የም​ት​ሠራ ነፍስ እር​ስዋ ትሞ​ታ​ለች።


የቆሬ ልጆች ግን አል​ሞ​ቱም።


ንጉ​ሡም፥ “አቤ​ሜ​ሌክ ሆይ! አን​ተና የአ​ባ​ትህ ቤት ሁሉ ፈጽ​ማ​ችሁ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ” አለ።