ዘዳግም 24:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለባልንጀራህ ባበደርኸው ጊዜ መያዣውን ልትወስድ ወደ ቤቱ አትግባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንኛውንም ነገር ለባልንጀራህ ስታበድር መያዣ አድርጎ የሚሰጥህን ለመቀበል ወደ ቤቱ አትግባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ማናቸውንም ነገር ለባልንጀራህ ስታበድር መያዣ አድርጎ የሚሰጥህን ለመቀበል ወደ ቤቱ አትግባ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለአንድ ሰው አንዳች ነገር በምታበድርበት ጊዜ መያዣ ይሰጥህ ዘንድ ዘለህ ወደ ቤቱ አትግባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለባልንጀራህ ባበደርኸው ጊዜ መያዣውን ልትወስድ ወደ ቤቱ አትግባ። |
ልብሱ ነውና፥ ዕርቃኑንም የሚሸፍንበት ይህ ብቻ ነውና፤ የሚተኛበትም ሌላ የለውምና፤ ወደ እኔም ቢጮኽ ፈጥኜ እሰማዋለሁ፤ መሓሪ ነኝና።