La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 23:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዘ​መ​ንህ ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሰላም እን​ደ​ሚ​ገ​ባ​ቸው አታ​ና​ግ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ሰላምን ለእነርሱ አትመኝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዘመንህ ሁሉ ለዘለዓለም ሰላምና ልማት ለእነርሱ አትሻ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በምትኖርበት ዘመን ሁሉ እነዚህ ሕዝቦች ባለጸጎች ሆነው በሰላም እንዲኖሩ አትርዳቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዘመንህ ሁሉ ለዘላለም ሰላምና ልማት ለእነርሱ አትሻ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 23:6
9 Referencias Cruzadas  

በው​ስ​ጥ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ አው​ጥቶ በመ​ጋ​ዝና በብ​ረት መቈ​ፈ​ሪያ በብ​ረት መጥ​ረ​ቢ​ያም ሥር አኖ​ራ​ቸው፤ በሸ​ክላ ጡብ እቶ​ንም አሳ​ለ​ፋ​ቸው። በአ​ሞን ልጆች ከተ​ሞች ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረገ። ዳዊ​ትም፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ።


ምና​ል​ባት መከ​ራ​ዬን አይቶ ስለ ርግ​ማኑ በዚህ ቀን መል​ካም ይመ​ል​ስ​ል​ኛል” አላ​ቸው።


ዳዊ​ትም ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን መታ፤ በም​ድ​ርም ጥሎ በገ​መድ ሰፈ​ራ​ቸው፤ በሁ​ለ​ትም ገመድ ለሞት፥ በአ​ን​ድም ገመድ ለሕ​ይ​ወት ሰፈ​ራ​ቸው፤ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት።


አሁ​ንም ትበ​ረቱ ዘንድ፥ የም​ድ​ሩ​ንም ፍሬ ትበሉ ዘንድ፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይወ​ር​ሱ​አት ዘንድ፥ ሴቶ​ችን ልጆ​ቻ​ች​ሁን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው አት​ስጡ፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ችሁ አት​ው​ሰዱ፤ ሰላ​ማ​ቸ​ው​ንና ደኅ​ን​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አትሹ።


ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፥ የቢዖርም ልጅ በለዓም የመለሰለትን አሁን አስብ፥ የእግዚአብሔርንም የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድ ከሰጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ አስብ።


ባላ​ቅም በበ​ለ​ዓም ላይ ተቈጣ፤ እጆ​ቹ​ንም አጨ​በ​ጨበ፤ ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን አለው፦ ጠላ​ቶ​ችን ትረ​ግም ዘንድ ጠራ​ሁህ፥


ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ወደ​ዳ​ችሁ፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን መሐላ ስለ ጠበቀ፥ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽኑ እጅ፥ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ አወ​ጣ​ችሁ፤ ከባ​ር​ነ​ትም ቤት ከግ​ብፅ ንጉሥ ከፈ​ር​ዖን እጅ አዳ​ና​ችሁ።