ዘዳግም 23:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ባልንጀራህ የወይን ቦታ በገባህ ጊዜ እስክትጠግብ ድረስ ከወይኑ ብላ፤ ወደ ዕቃህ ግን ከእርሱ ምንም አታግባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ባልንጀራህ ዕርሻ በምትገባበት ጊዜ፣ እሸት መቅጠፍ ትችላለህ፤ በሰብሉ ላይ ግን ማጭድ አታሳርፍበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ባልንጀራህ እርሻ በገባህ ጊዜ እሸቱን በእጅህ ቀጥፈህ ብላ፥ ወደ አልታጨደው ወደ ባልንጀራህ እህል ግን ማጭድ አታስገባ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንድ ሰው የእህል ማሳ ውስጥ በምታልፍበትም ጊዜ እሸቱን በእጅህ እየቈረጥህ መብላት ትችላለህ፤ ነገር ግን ሰብሉን አጭደህ አትውሰድ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ባልንጀራህ እርሻ በገባህ ጊዜ እሸቱን በእጅህ ቀጥፈህ ብላ፤ ወዳልታጨደው ወደ ባልንጀራህ እህል ግን ማጭድ አታግባ። |
“ወደ ባልንጀራህ እርሻ በገባህ ጊዜ እሸቱን በእጅህ ቀጥፈህ ብላ፤ ወዳልታጨደው ወደ ባልንጀራህ እህል ግን ማጭድ አታግባ።