Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 24:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “አንድ ሰው ሴትን ወስዶ ቢያ​ገባ፥ የእ​ፍ​ረት ነገር ስላ​ገ​ኘ​ባት በእ​ርሱ ዘንድ ሞገስ ባታ​ገኝ፥ የፍ​ች​ዋን ጽሕ​ፈት ጽፎ በእ​ጅዋ ይስ​ጣት፤ ከቤ​ቱም ይስ​ደ​ዳት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 አንድ ሰው አንዲት ሴት ካገባ በኋላ፣ አሳፋሪ ነገር አግኝቶባት ባይደሰትባት፣ የፍች ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ አስወጥቶ ይስደዳት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “አንድ ሰው አንዲት ሴት ካገባት በኋላ፥ አሳፋሪ ነገር አግኝቶባት ባይደሰትባት፥ የፍቺ ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ አስወጥቶ ይስደዳት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “አንድ ሰው አንዲት ሴት ካገባ በኋላ እርስዋን የማይወድበትን ነገር በማግኘቱ ቢጠላት የፍች የምስክር ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ ያባርራታል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ሰው ሴትን ወስዶ ቢያገባ፥ የእፍረት ነገር ስላገኘባት በእርሱ ዘንድ ሞገስ ባታገኝ፥ የፍችዋን ጽሕፈት ጽፎ በእጅዋ ይስጣት፥ ከቤቱም ይስደዳት።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 24:1
19 Referencias Cruzadas  

ከእ​ር​ስ​ዋም ሌላ ቢያ​ገባ፥ ቀለ​ብ​ዋን፥ ልብ​ስ​ዋ​ንም፥ ለጋ​ብ​ቻ​ዋም ተገ​ቢ​ውን ይስ​ጣት፤ እን​ዳ​ል​በ​ደ​ላ​ትም ምስ​ክር ያሰ​ማ​ባት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እና​ታ​ች​ሁን የፈ​ታ​ሁ​በት የፍ​ችዋ ደብ​ዳቤ የት አለ? ወይስ እና​ን​ተን የሸ​ጥሁ ከአ​በ​ዳ​ሪ​ዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ተሸ​ጣ​ች​ኋል፤ ስለ በደ​ላ​ች​ሁም እና​ታ​ችሁ ተፈ​ት​ታ​ለች።


“ሰው ሚስ​ቱን ቢፈታ፥ ከእ​ር​ሱም ዘንድ ሄዳ ሌላ ወንድ ብታ​ገባ፥ በውኑ ደግሞ ወደ እርሱ ትመ​ለ​ሳ​ለ​ችን? ያች ሴት እጅግ የረ​ከ​ሰች አይ​ደ​ለ​ች​ምን? አን​ቺም ከብዙ እረ​ኞች ጋር አመ​ን​ዝ​ረ​ሻል፤ ወደ እኔም ትመ​ለ​ሻ​ለ​ሽን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከዳ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም እስ​ራ​ኤል እን​ዳ​መ​ነ​ዘ​ረች አየሁ፤ የፍ​ች​ዋ​ንም ደብ​ዳቤ በእ​ጅዋ ሰጥቼ ሰደ​ድ​ኋት፤ ጎስ​ቋላ እኅቷ ይሁዳ ግን በዚያ አል​ፈ​ራ​ችም፤ እር​ስ​ዋም ደግሞ ሄዳ አመ​ነ​ዘ​ረች።


መፋታትን እጠላለሁ፥ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፥ ልብሱንም በግፍ ሥራ የሚከድነውን ሰው እጠላለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ስለዚህ እንዳታታልሉ መንፈሳችሁን ጠብቁ።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ የማ​ን​ኛ​ውም ሰው ሚስት ከእ​ርሱ ፈቀቅ ብትል፥ በእ​ር​ሱም ላይ ብት​በ​ድል፥


ራስ​ዋን ያላ​ረ​ከ​ሰች እንደ ሆነች፥ ያለ ነው​ርም እንደ ሆነች፥ ያነ​ጻ​ታል፤ ልጆ​ች​ንም ትወ​ል​ዳ​ለች።


እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ።


“ሚስ​ቱን ፈትቶ ሌላ​ዪ​ቱን የሚ​ያ​ገባ ሁሉ ያመ​ነ​ዝ​ራል፤ ባልዋ የፈ​ታ​ት​ንም የሚ​ያ​ገባ ያመ​ነ​ዝ​ራል።


“ለአ​ንድ ሰው አን​ዲቱ የተ​ወ​ደ​ደች፥ አን​ዲ​ቱም የተ​ጠ​ላች ሁለት ሚስ​ቶች ቢኖ​ሩት፥ ለእ​ር​ሱም የተ​ወ​ደ​ደ​ችው፥ ደግ​ሞም የተ​ጠ​ላ​ችው ልጆ​ችን ቢወ​ልዱ፥ በኵ​ሩም ከተ​ጠ​ላ​ችው ሚስት የተ​ወ​ለ​ደው ልጅ ቢሆን፥


“ማና​ቸ​ውም ሰው ሚስት ቢያ​ገባ፥ አብ​ሮ​አ​ትም ከኖረ በኋላ ቢጠ​ላት፥


በእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ላይ ክፉ ስም አም​ጥ​ቶ​አ​ልና መቶ የብር ሰቅል ያስ​ከ​ፍ​ሉት፤ ለብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት ይስ​ጡት፤ እር​ስ​ዋም ሚስት ትሁ​ነው፤ በዕ​ድ​ሜ​ውም ዘመን ሁሉ ሊፈ​ታት አይ​ገ​ባ​ውም።


ያ የደ​ፈ​ራት ሰው አምሳ የብር ሰቅል ለብ​ላ​ቴ​ና​ዪቱ አባት ይስጥ፤ አስ​ነ​ው​ሮ​አ​ታ​ልና ሚስት ትሁ​ነው፤ በዕ​ድ​ሜ​ውም ዘመን ሁሉ ሊፈ​ታት አይ​ገ​ባ​ውም።


ከቤ​ቱም ከወ​ጣች በኋላ ሌላ ወንድ ብታ​ገባ፥


ሁለ​ተ​ኛ​ውም ባል ቢጠ​ላት፥ የፍ​ች​ዋ​ንም ጽሕ​ፈት ጽፎ በእ​ጅዋ ቢሰ​ጣት ፥ ከቤ​ቱም ቢሰ​ድ​ዳት፥ ወይም ሚስት አድ​ርጎ ያገ​ባት ሁለ​ተ​ኛው ባልዋ ቢሞት፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos