እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
ዘዳግም 22:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወንድምህ አህያው ወይም በሬው በመንገድ ወድቆ ብታይ ቸል አትበላቸው፤ ነገር ግን ከእርሱ ጋር ሆነህ አነሣሣው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወንድምህ አህያ ወይም በሬ መንገድ ላይ ወድቆ ብታየው፣ በእግሩ እንዲቆምለት ርዳው እንጂ ዐልፈኸው አትሂድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንድምህ አህያ ወይም በሬው በመንገድ ወድቆ ብታይ ከእርሱ ጋር ሆነህ በማንሣት እርዳው እንጂ ቸል አትበለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤላዊ ወገንህ አህያ ወይም በሬ መንገድ ላይ ወድቆ ብታይ ዝም ብለህ አትለፍ፤ ቆሞ እንዲሄድ እንስሳውን በማንሣት እርዳው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወንድምህ አህያ ወይም በሬው በመንገድ ወድቆ ብታይ ከእርሱ ጋር ሆነህ አነሣሣው እንጂ ቸል አትበለው። |
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
እኔ ግን እጥፍ ድርብ አወጣለሁ፤ ስለ ሕይወታችሁም ሰውነቴን አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እናንተንም እጅግ ብወዳችሁ ራሴን ወደድሁ።
አህያውም ቢሆን፥ በሬውም ቢሆን፥ ወይም ልብሱ ቢሆን እንዲሁ ታደርጋለህ፤ እንዲሁም በወንድምህ በጠፋበት ነገር ሁሉ ባገኘኸው ጊዜ ታደርጋለህ፤ ቸል ልትለው አይገባህም።
“ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፤ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ፤ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና።
ወንድሞች ሆይ! እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዐት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።