ዘዳግም 20:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ አሳልፎ በሰጣት ጊዜ፥ በእርስዋ ያሉትን ወንዶች ሁሉ በሰይፍ ስለት ትገድላቸዋለህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር አሳልፎ በእጅህ በሰጠህ ጊዜ፣ በውስጧ ያሉትን ወንዶች በሙሉ በሰይፍ ግደላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላክህ ጌታ አሳልፎ በእጅህ በሰጠህ ጊዜ፥ በውስጧ ያሉትን ወንዶች በሙሉ በሰይፍ ግደላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክህ እግዚአብሔር ከተማይቱን ለአንተ አሳልፎ በሚሰጥበት ጊዜ በውስጥዋ የሚገኙትን ወንዶች ሁሉ ግደል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህም እግዚአብሔር በእጅህ አሳልፎ በሰጣት ጊዜ፥ በእርስዋ ያሉትን ወንዶች ሁሉ በሰይፍ ስለት ትገድላቸዋለህ፤ |