“ከቄድሞትም ምድረ በዳ የሰላምን ቃል ይነግሩት ዘንድ ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን እንዲህ ብዬ መልእክተኞችን ላክሁ፦
ዘዳግም 2:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘በሀገርህ ላይ ልለፍ፤ በአውራ ጎዳና እሄዳለሁ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አልተላለፍም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በአገርህ አቋርጠን እንድናልፍ ፍቀድልን፤ ከዋናው መንገድ አንወጣም፤ ቀኝም ግራም አንልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘በአገርህ ላይ ልለፍ፥ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ሳልል አውራ ጎዳናውን ይዤ እሄዳለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘በእናንተ አገር በኩል አልፈን እንድንሄድ ፍቀድልን፤ ከመንገዱ ሳንወጣና ወደ ቀኝም ወደ ግራም ሳንል በቀጥታ እንሄዳለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአውራ ጎዳና እሄዳለሁ፥ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አልተላለፍም። |
“ከቄድሞትም ምድረ በዳ የሰላምን ቃል ይነግሩት ዘንድ ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን እንዲህ ብዬ መልእክተኞችን ላክሁ፦
እስራኤልም ወደ አሞራዊው ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን መልእክተኞችን ላከ፤ እስራኤልም፦ ‘በምድርህ በኩል ወደ ስፍራችን፥ እባክህ፥ አሳልፈን’ አለው።