La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 2:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለሎ​ጥም ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ ከአ​ሞን ልጆች ምድር ርስት አል​ሰ​ጥ​ህ​ምና በአ​ሞን ልጆች አቅ​ራ​ቢያ ስት​ደ​ርስ አት​ጣ​ላ​ቸው፤ አት​ው​ጋ​ቸ​ውም።’

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከየትኛውም የአሞናውያን ምድር ለእናንተ ርስት ስለማልሰጣችሁ፣ አሞናውያን ዘንድ በደረሳችሁ ጊዜ አታስቸግሯቸው፤ ለጦርነትም አታነሣሧቸው። ያን ቦታ ርስት አድርጌ ለሎጥ ዘሮች ሰጥቻቸዋለሁ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በአሞን ልጆች አቅራቢያ ስትደርስ፥ ለሎጥም ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከአሞን ልጆች ምድር ርስት አልሰጥህምና፥ አትጣላቸው አትውጋቸውም።’”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህም በኋላ የሎጥ ዘሮች ወደሚኖሩበት ወደ ዐሞናውያን ምድር ትቃረባላችሁ፤ እነርሱንም አታስቸግሩአቸው፤ ወይም ከእነርሱ ጋር ጦርነት ለመግጠም አታነሣሡአቸው፤ ለእነርሱ ከሰጠኋት ምድር ለእናንተ ምንም አልሰጣችሁም።’ ”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለሎጥም ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከአሞን ልጆች ምድር ርስት አልሰጥህምና በአሞን ልጆች አቅራቢያ ስትደርስ አትጣላቸው አትውጋቸውም።

Ver Capítulo



ዘዳግም 2:19
8 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም እነሆ፥ እስ​ራ​ኤል ከግ​ብዕ ምድር በወጡ ጊዜ ያል​ፉ​ባ​ቸው ዘንድ ያል​ፈ​ቀ​ድ​ህ​ላ​ቸው የአ​ሞ​ንና የሞ​ዓብ ልጆች፥ የሴ​ይ​ርም ተራራ ሰዎች እን​ዳ​ያ​ጠ​ፉ​አ​ቸው ከእ​ነ​ርሱ ፈቀቅ ብለው ነበር።


ስለ ሞዓብ የተ​ነ​ገረ ቃል። ሞዓብ በሌ​ሊት ትጠ​ፋ​ለች፤ የሞ​ዓ​ብም ምሽግ በሌ​ሊት ይፈ​ር​ሳል።


ዳሩ ግን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘን ወደ አሞን ልጆች ምድር፥ በያ​ቦ​ቅም ወንዝ አጠ​ገብ ወደ አለው ስፍራ ሁሉ፥ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም ሀገር ወደ አሉ ከተ​ሞች አል​ደ​ረ​ስ​ንም።


የሴ​ይ​ርን ተራራ ለዔ​ሳው ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከም​ድ​ራ​ቸው የጫማ መር​ገጫ ታህል እን​ኳን አል​ሰ​ጣ​ች​ሁ​ምና አት​ጣ​ሉ​አ​ቸው።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ እኔ አሮ​ኤ​ርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ ከም​ድሩ ርስት አል​ሰ​ጣ​ች​ሁ​ምና ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን አት​ጣላ፤ በሰ​ል​ፍም አት​ው​ጋ​ቸው።


በሐ​ሴ​ቦ​ንም የነ​ገሠ የአ​ሞ​ሬ​ዎን ንጉሥ የሴ​ዎን ከተ​ሞ​ችን ሁሉ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፥