La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 19:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ሰው ግን ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ቢጠላ፥ ቢሸ​ም​ቅ​በ​ትም፥ በእ​ር​ሱም ላይ ቢነሣ፥ ቢገ​ድ​ለ​ውም፥ ከእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ቢማ​ጠን፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይሁን እንጂ አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢጠላው፣ አድፍጦ ጥቃት ቢያደርስበት፣ ቢገድለውና ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ቢሸሽ፣

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ይሁን እንጂ አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢጠላው፥ አድፍጦ ጥቃት ቢያደርስበት፥ ቢገድለውና፥ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ቢሸሽ፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ነገር ግን አንድ ሰው በጠላትነት ተነሣሥቶ በመሸመቅ ሆን ብሎ በጭካኔ ሌላውን ሰው ከገደለ በኋላ ሕይወቱን ለማትረፍ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ቢሸሽ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሰው ግን ባልንጀራውን ቢጠላ፥ ቢሸምቅበትም፥ ተነሥቶም እስኪሞት ድረስ ቢመታው፥ ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ቢሸሽ፥

Ver Capítulo



ዘዳግም 19:11
9 Referencias Cruzadas  

ነፍ​ሳ​ችሁ ያለ​ች​በ​ትን ደማ​ች​ሁን ከአ​ራ​ዊት ሁሉ እጅ እሻ​ዋ​ለሁ፤ ከሰ​ውም እጅ፥ ከሰው ወን​ድም እጅ፥ የሰ​ውን ነፍስ እሻ​ለሁ።


የሰ​ውን ደም የሚ​ያ​ፈ​ስስ ሁሉ ስለ​ዚያ ደም ፈንታ ደሙ ይፈ​ስ​ሳል፤ ሰውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መልክ ፈጥ​ሬ​ዋ​ለ​ሁና።


ጠላ​ቱም ባይ​ሆን፥ ክፉም ያደ​ር​ግ​በት ዘንድ ባይሻ፥ ማኅ​በሩ በመ​ቺ​ውና በባለ ደሙ መካ​ከል ፍር​ድን እን​ደ​ዚህ ይፍ​ረዱ፤


የከ​ተ​ማው ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ይል​ካሉ፤ ከዚ​ያም ይይ​ዙ​ታል። በባ​ለ​ደ​ሙም እጅ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ታል፤ ይሞ​ታ​ልም።


“ባል​ን​ጀ​ራ​ውን በተ​ን​ኰል የሚ​መታ ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።


ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ።