በይሁዳም ከተሞች የሚኖሩ የእስራኤልና የይሁዳ ልጆች የበሬዉንና የበጉን፥ የፍየሉንም ዐሥራት አመጡ፤ ለአምላካቸው ለእግዚአብሔርም ቀደሱት፤ ከምረውም አኖሩት።
ዘዳግም 14:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በየሦስተኛው ዓመት መጨረሻ በዚያ ዓመት የፍሬህን ዐሥራት ሁሉ አምጥተህ በከተማዎችህ ውስጥ ታኖረዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በየሦስት ዓመቱ መጨረሻ የዚያን ዓመት ሰብል ዐሥራት በሙሉ አውጥተህ በከተሞችህ ውስጥ አከማች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በየሦስት ዓመቱም መጨረሻ የዚያን ዓመት ሰብል አሥራት በሙሉ አውጥተህ በከተሞችህ ውስጥ አከማች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየሦስተኛው ዓመት መጨረሻ ላይ ከእርሻችሁ ሰብል ሁሉ ከዐሥር አንዱን እያወጣችሁ በከተሞቻችሁ አከማቹ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በየሦስተኛው ዓመት መጨረሻ በዚያ ዓመት የፍሬህን አሥራት ሁሉ አምጥተህ በአገርህ ደጅ ውስጥ ታኖረዋለህ፤ |
በይሁዳም ከተሞች የሚኖሩ የእስራኤልና የይሁዳ ልጆች የበሬዉንና የበጉን፥ የፍየሉንም ዐሥራት አመጡ፤ ለአምላካቸው ለእግዚአብሔርም ቀደሱት፤ ከምረውም አኖሩት።
“ወደ ቤቴል ገብታችሁ ኀጢአትን ሠራችሁ፤ በጌልገላም ኀጢአትን አበዛችሁ፤ በየማለዳውም መሥዋዕታችሁን፥ በየሦስተኛውም ቀን ዐሥራታችሁን አቀረባችሁ፤