በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ፥ በናባጥም ልጅ በኢዮርብዓም መንገድ እስራኤልንም ባሳተበት ኀጢአት ሄደ።
ዘዳግም 12:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን በሚታይህ ስፍራ ሁሉ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን በፈለግኸው ስፍራ ሁሉ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን በፈለግኸው ስፍራ ሁሉ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚቃጠል መሥዋዕትህን በማናቸውም ቦታ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን በሚታይህ ስፍራ ሁሉ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ። |
በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ፥ በናባጥም ልጅ በኢዮርብዓም መንገድ እስራኤልንም ባሳተበት ኀጢአት ሄደ።
በኮረብታ ላይ የነበሩትን መስገጃዎች ግን ከእስራኤል አላራቀም። ገና በእስራኤል ዘንድ እስከ አሁን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ የአሳ ልብ በዘመኑ ሁሉ ፍጹም ነበረ።
በዚያን ጊዜ አምላካችሁ እግዚአብሔር ስሙ ይጠራበት ዘንድ ወደዚያ ወደ መረጠው ስፍራ፥ እኔ የማዝዛችሁን ሁሉ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ቍርባናችሁንም፥ ዐሥራታችሁንም፥ ከእጃችሁ ሥራ ቀዳምያቱን የተመረጠውንም መባችሁን ሁሉ፥ ለአምላካችሁም የተሳላችሁትን ሁሉ ውሰዱ።
ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ከነገዶችህ ከአንዱ ዘንድ በመረጠው ስፍራ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን አቅርብ፤ በዚያም ዛሬ እኔ የማዝዝህን ሁሉ አድርግ።
ነገር ግን አምላካችሁ እግዚአብሔር ከከተሞቻችሁ ሁሉ በአንዱ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመረጠውን ስፍራ ትሻላችሁ፤ ወደዚያም ትመጣላችሁ።
ወደዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ቍርባናችሁንም፥ ዐሥራታችሁንም፥ ቀዳምያታችሁን፥ ስዕለታችሁንም፥ በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትን፥ የላማችሁንና የበጋችሁንም በኵራት ውሰዱ።
በገለዓድም ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ጋድ ልጆች፥ ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ ደረሱ፤ እንዲህም ብለው ነገሩአቸው
በድንኳኑ ፊት ካለው ከአምላካችን ከእግዚአብሔር መሠዊያ ሌላ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለሰላም መሥዋዕት፥ ለደኅንነት መሥዋዕትም የሚሆን መሠዊያን የሠራነው በእግዚአብሔር ላይ በማመፅ እግዚአብሔርንም ዛሬ መከተልን ለመተው በማለት እንደ ሆነ ይህ ከእኛ ይራቅ።”