La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 11:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው፤ በቤ​ትም ሲቀ​መጡ፥ በመ​ን​ገ​ድም ሲሄዱ፥ ሲተ​ኙም፥ ሲነ​ሡም እን​ዲ​ነ​ጋ​ገ​ሩ​በት፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ልጆቻችሁንም አስተምሯቸው፤ በቤትህ ስትቀመጥ፣ በመንገድም ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሣም ስለ እነርሱ ተናገር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ልጆቻችሁንም አስተምሯቸው፤ ቤት ስትቀመጥ፥ መንገድ ስትሄድ፥ ስትተኛና ስትነሣ ስለዚህ አጫውታቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለልጆቻችሁም አስተምሩአቸው፤ በቤት በምትቀመጡበት ጊዜ፥ ወይም ስትሄዱ፥ ዕረፍት በምታደርጉበትም ሆነ በምትሠሩበት ጊዜ ሁሉ ስለ እነርሱ ተነጋገሩ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ልጆቻችሁንም አስተምሩአቸው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም ስትነሣም አጫውቱአቸው።

Ver Capítulo



ዘዳግም 11:19
12 Referencias Cruzadas  

እነ​ርሱ የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩ​ህና የሚ​ነ​ግ​ሩህ፥ ቃል​ንም ከል​ባ​ቸው የሚ​ያ​ወጡ አይ​ደ​ሉ​ምን?


የዐ​መፃ ምስ​ክ​ሮች ተነ​ሡ​ብኝ፥ የማ​ላ​ው​ቀ​ንም በእኔ ላይ ተና​ገሩ።


ለጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቻ​ች​ንም ስድብ ሆንን፥ በዙ​ሪ​ያ​ች​ንም ላሉ ሣቅና መዘ​በቻ።


ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ብትቀበል፥ ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት፥


ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።


እኔ ዛሬ እን​ደ​ማ​ደ​ርግ ሕያ​ዋን ብቻ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤ ከዛሬ ጀምሮ ጽድ​ቅ​ህን የሚ​ና​ገሩ ልጆ​ችን እወ​ል​ዳ​ለሁ።


እና​ን​ተም አባ​ቶች ሆይ፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተግ​ሣ​ጽና ምክር አሳ​ድ​ጉ​አ​ቸው እንጂ አታ​ስ​ቈ​ጡ​አ​ቸው።


እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ይጠ​ብ​ቁና ያደ​ርጉ ዘንድ ልጆ​ቻ​ች​ሁን እን​ድ​ታ​ዝ​ዙ​በት ዛሬ የም​መ​ሰ​ክ​ር​ላ​ች​ሁን ቃል ሁሉ በል​ባ​ችሁ አኑ​ሩት።


ለል​ጆ​ች​ህም አስ​ተ​ም​ረው፤ በቤ​ት​ህም ስት​ቀ​መጥ፥ በመ​ን​ገ​ድም ስት​ሄድ፥ ስት​ተ​ኛም፥ ስት​ነ​ሣም አስ​ተ​ም​ረው።