ዘዳግም 1:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እናንተም፦ እግዚአብሔርን በድለናል፤ አምላካችን እግዚአብሔር እንዳዘዘን ሁሉ እንወጣለን፤ እንዋጋማለን ብላችሁ መለሳችሁልኝ። ከእናንተም ሰው ሁሉ የጦር መሣሪያውን ያዘ፤ ወደ ተራራም ወጣችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ፣ “በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርተናል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ባዘዘንም መሠረት ወጥተን እንዋጋለን” ብላችሁ መለሳችሁልኝ። ወደ ተራራማው አገር መሄድ ቀላል መስሎ ስለ ታያችሁ፣ እያንዳንዳችሁ የጦር መሣሪያችሁን ታጥቃችሁ ተነሣችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እናንተም፦ ‘ጌታን በድለናል፥ ጌታ አምላካችን ልክ እንዳዘዘን፥ እንወጣለን እንዋጋለንም’ ብላችሁ መለሳችሁልኝ። ከእናንተም ሰው ሁሉ የጦር መሣሪያውን ያዘ፥ ወደ ተራራማውም አገር መውጣትን አቀለላችሁት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እናንተም ‘ሙሴ ሆይ፥ እኛ እግዚአብሔርን በድለናል፤ አሁን ግን አምላካችን እግዚአብሔር ባዘዘን መሠረት እንዋጋለን’ ብላችሁ መለሳችሁ፤ ኮረብታማይቱን አገር መውረር ቀላል መስሎአችሁ ከእናንተ እያንዳንዱ ለውጊያ ተዘጋጀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም፦ እግዚአብሔርን በድለናል፤ አምላካችን እግዚአብሔር እንዳዘዘን ሁሉ እንወጣለን፥ እንዋጋማለን ብላችሁ መለሳችሁልኝ። ከእናንተም ሰው ሁሉ የጦር መሣሪያውን ያዘ፥ ወደ ተራራማውም አገር መውጣትን አቀለላችሁት። |
በለዓምም የእግዚአብሔርን መልአክ፥ “በድያለሁ፤ አንተ በመንገድ ላይ በፊቴ እንደ ቆምህብኝ አላወቅሁም፤ እንግዲህ አሁን አትወድድ እንደሆነ እመለሳለሁ” አለው።